ስፓርት
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር 5 ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር አምስት ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።
በሳምንቱ የመክፈቻ ጨዋታ በመርሲሳይድ ደርቢ ሊቨርፑል ከኤቨርተን የሚያደርጉት ጨዋታ ቀን 9 ሰዓት ከ30 ይካሄዳል።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሶስት ጨዋታዎች ሲደረጉ አስቶንቪላ ከሳውዝሃምፕተን፣ ክሪስታል ፓላስ ከማንቼስተር ሲቲ እንዲሁም ብረንትፎርድ ከኒውካስትል ዩናይትድ ይጫወታሉ።
ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ደግሞ ማንቼስተር ዩናይትድ ኖቲንግሃም ፎረስትን በኦልድትራፎርድ የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡…
Read More...
ሀዲያ ሆሳዕና አዳማ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሀዲያ ሆሳዕና አዳማ ከተማን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
በድሬዳዋ ስታዲየም ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና ኢዮብ አለማየሁ እና በረከት ወ/ዮሐንስ ባስቆጠሯቸው ሁለት ግቦች ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
በተመሳሳይ ቀን 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ…
ኢትዮጵያ ቡና አርባ ምንጭ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ10ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና አርባ ምንጭ ከተማን 2 ለ 0 አሸነፈ፡፡
10 ሠዓት ላይ በተከናወነው ጨዋታ ለኢትዮጵያ ቡና የማሸነፊያ ግቦቹን ከዕረፍት መልስ ዲቫይን ዋቹኩዋ እና ኦካይ ጁል አስቆጥረዋል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 1 ሠዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 3…
አርሰናል ከማንቼስተር ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ14ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብሮች ሲደረጉ ምሽት 5 ሠዓት ከ15 ላይ አርሰናል በኤምሬትስ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል፡፡
በቡድኖቹ መካካል በተለይም ከፈረንጆቹ 1996 እስከ 2004 የነበረው ብርቱ ፉክክር÷ በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ቀደም ሲልም ሆነ ከዚያ በኋላ…
በአርባምንጭ ከተማ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር ታላቅ ሩጫ በአርባምንጭ ከተማ ተካሂዷል፡፡
የጎዳና ላይ ሩጫው በህዝብ ተሳትፎና በክልሉ መንግሥት ድጋፍ እየተገነባ ለሚገኘው የአርባ ምንጭ ዓለም ዓቀፍ ስታዲየም ግንባታ ገቢ ለማሰባሰብ እንዲሁም በከተማው የሚከበረውን የብሔር፣…
በጊኒ የእግር ኳስ ዳኛ ውሳኔን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት የ56 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በጊኒ የእግር ኳስ ዳኝነት ላይ የተላለፈን ውሳኔ ተከትሎ በተፈጠረ ግጭትና መረጋገጥ የ56 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡
በጊኒ ንዜርኮሬ ከተማ በተደረገ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ላቤ የተሰኘ የእግር ኳስ ክለብ ላይ የተላለፈ የዳኝነት ውሳኔን ተከትሎ ደጋፊዎች ድንጋይ መወርወር መጀመራቸው ተመላክቷል፡፡
ግጭቱን ለመቆጣጠርም…
የመቻል ስፖርተኞች በስፖርቱ ዘርፍ የኢትዮጵያ አደራ አለባቸው – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የመቻል ስፖርተኞች በስፖርቱ ዘርፍ ከተቋም ባለፈ የኢትዮጵያ አደራ አለባቸው ሲሉ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በናይጀሪያ አቡጃ በመላው አፍሪካ የጦር ሃይሎች ስፖርት ፌስቲቫል ተካፋይ ለነበረው የመቻል አትሌቲክስ ቡድን አቀባበል አድርገዋል።…