Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ሰላም ያስፈልጋታል – አቶ ብናልፍ አንዱዓለም

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከሁሉም በላይ ሰላም ያስፈልጋታል ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም ገለጹ፡፡

በአዲስ አበባ “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሐሳብ የሰላም ሩጫ ውድድር ተካሂዷል፡፡

በሰላም ሩጫው ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለምን ጨምሮ የፌደራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ አትሌቶችና ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።

በዚሁ ወቅት አቶ ብናልፍ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከሁሉም በላይ ሰላም ያስፈልጋታል፤ የሰላም ሩጫው ዋና ዓላማም የሰላም ፍላጎታችንን ከፍ አድርገን ለማሳየት ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እያሳካቻቸው ያሉትን ስኬቶች ለማስቀጠል፤ ሰላም በእጅጉ ያስፈልጋታል ብለዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች በበኩላቸው÷ የከተማችን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ የተጠበቀው ሕዝብን ያሳተፈ የሰላም ስራ በመሰራቱ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ይህን ሰላም አስጠብቆ ለመዝለቅ ሁሉም ሰው እያበረከተ ያለውን ድርሻ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.