Fana: At a Speed of Life!

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል ሰበሰቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ሠራተኞች የዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል ሰበሰቡ፡፡
ዩኒቨርሲቲው ሰብል ከመሰብሰብ በተጨማሪ አርሶ አደሮች ወቅቱ የሚጠይቀውን ምርት አምርተው ለገበያ እንዲያቀርቡ ለማድረግ የማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኝ÷ የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ሠራተኞች ላለፉት ሁለት ሳምንታት የዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል መሰብሰባቸውን ጠቁመው÷ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡
የሰብል በወቅቱ መሰብሰብ÷ ሰብልን ከብክነት ለመታደግ እንዲሁም በጦርነት ምክንያት የወደመውን ምርት በዳግም ሰብል እና በመስኖ በማካካስ ሊከሰት የሚችለውን የምግብ እጥረት ለመቅረፍ ይጠቅማል ብለዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች ለህልውና ዘመቻው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዚደንቱ÷ ዩኒቨርሲቲውም በመስኖ ለሚያለሙ አርሶ አደሮች ዘር፣ ማዳበሪያ እና ሙያዊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም አብራተዋል፡፡
ትራክተርና ኮምባይነር ገዝቶ ለማቅረብ ሥራ መጀመሩን ጠቁመዉ÷ ዛሬ ሰብሉ የተሰበሰበበት ማሳ በቀጣይ ቀናት በመስኖ ስንዴ ዘር ይሸፈናል ማታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.