ለመስኖ የሚውል መሬት በምንም ምክንያት ጾም አያድርም- ዶ/ር ይልቃል ከፋለ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ለመሥኖ የሚውል መሬት በምንም ምክንያት ጾም አያድርም ሲሉ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ተናገሩ፡፡
በአማራ ክልል በግብርናው ዘርፍ የተሠማሩ ባለሀብቶች ለመሥኖ ስንዴ ልማት በተመረጡ መሬቶች ላይ ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያስችል የምክክር መድረክ ለሁለተኛ ጊዜ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ÷ አሸባሪው ህወሃት በሰብል ልማት ምርታማነት ላይ ያደረሠውን ጉዳት ለማካካስ በዚህ አመት መሬት ጦም ማደር የለበትም ፤እስከዛሬ በተለያየ ምክንያት ወደ ልማት ያልገቡ መሬቶችም ሊለሙ ይገባል ብለዋል፡፡
አሸባሪውን ቡድን በመደምሰስ የኢትዮጵያን አንድነትና የአማራ ክልልን ህልወናና ሠላም ማስጠበቅ ቀዳሚው ተግባራችን ነው ያሉት ርዕሰ መሥተዳደሩ ሁለተኛው የትግል ግንባር የምርትና ምርታማነትን ማሣደግና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በየደረጃው ያሉ የግብርና ቢሮ ጽህፈት ቤቶች የመሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ተቋማት በተቀናጀ መልኩ ለአልሚ አካላት ምቹ ሁኔታ ሊፈጥሩ ይገባል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሀይለ ማርያም ከፍያለው ÷በክልሉ ምርትና ምርታማነትን ለማሣደግ የተለያዩ ስልቶች ተቀይሰው እየተሠሩ ይገኛሉ ያሉ ሲሆን ÷ በዚህም በመሥኖ ስንዴ ልማት ባለሀብቶችን ማሣተፍ አንዱ ነው ብለዋል፡፡
በአለባቸው አባተ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!