Fana: At a Speed of Life!

40 ሚሊየን ሊትር ዘይት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ቤት ሊገባ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሞኑን በዘይት ምርቶች ላይ የተስተዋለው የዋጋ ጭማሪ የዓለም አቀፍ ገበያው ላይ በመጣው ለውጥ ምክንያት መሆኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህ ለውጥ ምክንያት የተፈጠረውን የምርት እጥረት መነሻ በማድረግ በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ የተፈጠረው ውዥንብር የዋጋ ጭማሪውን አባብሶታል ተብሏል።

መንግስት የአቅርቦት እጥረቱን ለማቃለል በአጭር ጊዜ መፍትሄ 40 ሚሊየን ሊትር ዘይት እንደሚያስገባ ተገልጿል።

በረዥም ጊዜ መፍትሄነት የምርት አቅርቦቱን እና ፍላጎቱን ማጣጣም እንዲቻል የገበያ ሁኔታውን የሚያጠና ቡድን መዋቀሩም ነው የተገለጸው።

በበርናባስ ተስፋዬ

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.