በአሸባሪው ህወሓት የተዘረፈው የወልድያ ተንቀሳቃሽ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህወሓት ቡድን ሙሉ በሙሉ ተነቅሎ የተወሰደው የወልድያ ተንቀሳቃሽ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ በአዲስ ለመተካት የሚያስችል የፕሮጀክት ግንባታ ሥራ ተጀምሯል።
የፕሮጀክቱ የሲቪል ሥራዎች ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ከፈለኝ እንደተናገሩት ፥ ፕሮጀክቱ ከዚህ በፊት ከነበረው ተንቀሳቃሽ ጣቢያ በተለየ መልኩ በቋሚነት የሚሠራ የማከፋፈያ ጣቢያ ይሆናል ብለዋል።
የፕሮጀክቱ የኤሌክትሮ – ሜካኒካል ሥራዎች የሳይት አስተባባሪ አቶ አሊ ከሚል በበኩላቸው ÷ ጣቢያው አንድ ባለ 63 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመር እንደሚገጠምለትና ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ 5 ባለ 33 ኪሎ ቮልት እና 6 ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጭ መስመሮች እንደሚኖሩት ተናግረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያው አገልግሎት ያገኙ ለነበሩ እንደ ጭፍራ፣ ጎብየ፣ ቆቦ፣ ሮቢት እና ሌሎች የሰሜን ወሎ ዞን አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል።
የፕሮጀክቱ የግንባታ ሥራ በተቋሙ ትራንስሚሽንና ሰብስቴሽን ኮንስራክሽን የራስ ኃይል ቢሮ በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን ፥ ለሥራው የግብዓት አቅርቦቱን ሳይጨምር ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ዕቅድ መያዙን ለማወቅ ተችሏል።
ፕሮጀክቱን በተያዘው በጀት ዓመት ለማጠናቀቅም ዕቅድ መያዙን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሙሉ በሙሉ በአሸባሪ ቡድኑ የተወሰደውን የወልዲያ ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያን ወደነበረበት ለመመለስ እና በአዳዲስ ዕቃዎች ለመተካት በትንሹ እስከ 200 ሚሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ከዚህ በፊት መገለጹ ይታወሳል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!