Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ተወካዮች ልዑክ ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ተወካዮች ልዑክ ጋር ተወይዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከእስያ ጉብኝታቸው ማምሻውን ተመልሰዋል፡፡

በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሦስት ቀናት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን ካጠናቀቁት የሳዑዲ አረቢያ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ተወካዮች ልዑክ ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ በቤቶች ልማት፣ በቱሪዝም እና በግብርና በተለይም በሀገር ውስጥ የማዳበሪያ ምርት ላይ ያተኮረ እንደነበር ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

79 ኢንቨስተሮችን ያካተተው ከፍተኛ ልዑክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የሳዑዲ አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሰልማን በሕዳር ወር በሳዑዲ – አፍሪካ ጉባኤ ወቅት ያደረጉትን የሁለትዮሽ ውይይት ተከትሎ የተከናወነ እንደሆነም ተጠቅሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.