አቶ እንዳሻው በሃድያ ዞን የተገነቡ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን መረቁ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው በክልሉ ሃድያ ዞን የተገነቡ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን መርቀዋል፡፡
በምረቃ መርሐ ግብሩ የክልሉ ዋና የመንግስት ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አንተነህ ፍቃዱ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው በሀድያ ዞን ዱና ወረዳ የተገነባውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት መርቀው ከፍተዋል፡፡
የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ከ40 ሺህ በላይ የአካባቢው ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይ በተለያዩ አካባቢዎች ግንባታቸው የተጠናቀቁ ሌሎች ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት እንደሚያደርጉም ተጠቁሟል፡፡