Fana: At a Speed of Life!

የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ ረገድ ለውጦች እየተመዘገቡ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ ረገድ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ ገለጸ።

የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ከቅርጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ጋር በመሆን “ጠንካራና ውጤታማ አደረጃጀት ለራዕያችን ስኬት” በሚል መሪ ሀሳብ የስድስት ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል።

በሚኒስትር ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በመድረኩ እንዳሉት፤ የሰላም፣ የልማት እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመመለስ ረገድ ለውጦች እየተመዘገቡ ነው።

የፓርቲው አሠራሮች እንዲከበሩ በማድረግ የአባላትን የፖለቲካዊ ጤንነት በማስጠበቅ፣ የአባላት ምልመላ ጥራት እንዲኖረው ማድረግ እና አደረጃጀቶች በእቅዳቸው ልክ እንዲመሩ እና ውጤት እንዲያመጡ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የፓርቲውን ውስጣዊ ጥራት ለማስጠበቅ የሚያግዙ አሰራሮችን ይበልጥ በማጎልበት ባሉን አባላት ብዛት ልክ ውስጣዊ ጤንነት በማረጋገጥ ተጽእኖ የመፍጠር እና ፈተናን የመቋቋም አቅማችንን ማሳደግ ጊዜው የሚጠይቀው ወሳኝ ተልእኮ ነው ብለዋል።

መድረኩ የመተዋወቅ ተሞክሮን የመለዋወጥ እና ቤተሰባዊ ቅርርብን በማጠናከር በክልሎች መካከል ተቀራራቢ አፈጻጸም ለማስመዝገብ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.