Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ከ120 ሺህ በላይ ተማሪዎች በምገባ መርሐ ግብር ይካተታሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በ2018 የትምህርት ዘመን ከ120 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በምገባ መርሐ ግብር ለማካተት ዝግጅት ተደርጓል አለ ።
‎የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ ደስታ ገነሜ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥ በክልሉ ተማሪዎችን በትምህርት ቤት ምገባ በማካተት የሚስተዋለውን የትምህርት ማቋረጥ ለማስቀረት እየተሰራ ነው፡፡።
ባለፈው የትምህርት ዘመን በክልሉ ከ44ሺ በላይ ተማሪዎችን በምገባ መርሐ ግብሩ ማካተት መቻሉን አስታውሰው፥ ምገባው ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ በመማር ማስተማር ላይ መሻሻሎች መኖራቸውን ነው የገለጹት፡፡
‎በምገባ ሂደቱ የሚስተዋሉ ክፈተቶችን መገምገሙን ያነሱት ኃላፊው፥ ህብረተሰቡ በዚህ የትውልድ አደራ መሳተፉን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሲሳይ ለገሰ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.