Fana: At a Speed of Life!

ዳንጎቴ ግሩፕ የተሻለ ልምድ ስላለው የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክሱ በዕቅዱ መሰረት ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዳንጎቴ ግሩፕ የተሻለ ልምድ ስላለው የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክሱ በዕቅዱ መሰረት ይጠናቀቃል አለ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክስ የድርሻ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈርሟል፡፡
ስምምነቱን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክሱ ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠርን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው።
የ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚፈስበት ፕሮጀክቱ በዓመት እስከ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የማምረት አቅም ያለው ነው ብለዋል።
በስምምነቱ መሰረት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ 40 በመቶ፤ ቀሪው 60 በመቶ የዳንጎቴ ግሩፕ ድርሻ መሆኑን ጠቁመዋል።
በ40 ወራት እንዲጠናቀቅ እቅድ የወጣለት ፕሮጀክት በሺዎች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን የሥራ እድል የሚፈጥር እንደሆነም አመልክተዋል።
ዳንጎቴ ግሩፕ በዘርፉ የተሻለ ልምድ ያለው በመሆኑ በተያዘው የጊዜ ዕቅድ መሰረት ፕሮጀክቱን እናጠናቅቃለን ነው ያሉት።
የማዳበሪያ ማምረቻ ኮምፕሌክሱ ማዳበሪያ ከማምረት በተጨማሪ በሌሎች ኢንዱስትሪዎች ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረውም አስረድተዋል።
በሶስና አለማየሁ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.