የክልል መስተዳድሮች አዲስ መንግስት የሚመሰርቱበት ቀን ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የክልል መስተዳድሮች አዲስ መንግሥት የሚመሰርቱበትን ቀን ይፋ አድርገዋል፡፡
በዚሁ መሠረት የአማራ ክልል፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል፣ የሲዳማ ክልል እና የጋምቤላ ክልል በቀጣይ ሳምንት አዲስ መንግስት እንደሚመሰርቱታውቋል፡፡
የአዲሱ መንግስት ምስረታ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል መስከረም 22፣ በጋምቤላ ክልል፣ በአማራ ክልል እና በሲዳማ ክልል መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚሆን ክልሎቹ አስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የአዲሱ መንግስት ምስረታ መስከረም 21 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚሆን አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!