Fana: At a Speed of Life!

ከኤሌክትሮኒክስ ንግድ ጋር ተያይዞ የዲጂታላይዜሽን ስራዎች እንዲያፋጠኑ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኤሌክትሮኒክስ የተሰጠ ማንኛውም መረጃ በወረቀት ከተሰጠ መረጃ ጋር እኩል ህጋዊ እንደሆነ ተገለጸ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር አብዮት ባዩ÷ ዜጎች የዲጂታል አገልግሎት ላይ እምነት ኖሯቸው እንዲጠቀሙ ለማድረግ የህግ ማዕቀፎ እየተዘጋጁ ስለመሆናቸው ገልጸዋል።

በቀጣይ የኤሌክትሮኒክስ ትራንዛክሽ አዋጅ፣ የኤሌክትሮኒክስ ትራንዛክሽን ረቂቅ ደንብ እና የግል ዴታ ጥበቃ አዋጅ ዙሪያ ከግሉ ዘርፍ የዲጂታል ቢዝነስ አንቀሳቃሾች ጋር ውይይት ተደርጓል፤ የሚመለከታቸው አካላትም በዘርፉ ያሉ ችግሮችን አንስተዋል፣ የመፍትሄ ሃሳብም እንደተመላከተ እና ግብዓት እንደተሰጠ ነው የታወቀው፡፡

የዘርፉ ተዋናዮች ከኤሌክትሮኒክስ ንግድ ጋር ተያይዞ ገቢዎች የዲጂታላይዜሽን ስራውን እንዲያፋጥን ጠይቀዋል።

በተለይ ከኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝና የኤሌክትሮኒክስ ታክስ ጋር ተያይዞ የተጠናከረ ስራ መስራት እንደሚጠይቅ አንስተዋል።

አሁን በረቂቅ ደረጃ ያለው የግል ዴታ ጥበቃ አዋጁ ግለሰቦች በግል መረጃቸው ላይ ያላቸውን ዝርዝር መብትና ጥበቃ የሚደነግግ ይሆናል።

አዋጁን ተከትሎ ደንብና መመሪያ የማርቀቅ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.