Fana: At a Speed of Life!

ከ97 በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ያላገኙ የገጠር ከተሞች ተጠቃሚ ሆነዋል – የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ97 በላይ የገጠር ከተሞችን በባለፈው በጀት ዓመት የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ።

የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አቶ ማህተቤ አለሙ እንደገለጹት÷ ከ3 ሺህ 800 ኪሎ ሜትር በላይ የኤሌክትሪክ መስመር በ2013 በጀት ዓመት ተዘርግቷል፡፡

ከ 1 ሺህ 500 በላይ የትራንስፎርመር ተከላ ማካሄዱን የገለጸው ተቋሙ ÷በዚህም ከ134 ሺህ በላይ ቆጣሪዎችን በማገናኛት በርካታ የኅብረተሠብ ክፍሎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን ነው ያመላከተው፡፡

ተቋሙ ከ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማስገባቱን ገልጾ በሀገር አቀፍ ደረጃ ውጤታማ አፈጻጸም በማስመዝብ እውቅና እንደተሠጠውም ጠቁሟል።

በዘንድሮው ዓመትም የኃይል ማሻሻያ ኘሮጀክቶችን ወደ ስራ በማስገባትኤሌክትሪክ የማያገኙ የኅብረተሠብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራሁ ነው ብሏል።

በከድር መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.