Fana: At a Speed of Life!

30 ኩንታል በርበሬና ሽሮ ከባዕድ ነገሮች ቀላቅለው ለሽያጭ ያቀረቡ ግለሰቦች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን አረካ ከተማ ባዕድ ነገር በመቀላቀል እህል ሲፈጩ የተገኙ ወፍጮ ቤቶችን በማሸግ ባዕድ ነገር የተቀላቀለበት ሽሮና በርበሬ በፖሊስ ኤግዚቢትነት እንዲያዝ ተደርጓል።
በዚህ ሳምንት ብቻ 17 ኩንታል በርበሬ እና 13 ኩንታል ሽሮ በድምሩ 30 ኩንታል የሽሮና የበርበሬ እህሎች ጋር ባዕድ ነገር በመቀላቀል ሲፈጩና ሲያስፈጩ የተያዙ 2 የወፍጨ ባለቤቶችና 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ግለሰቦቹ በፖሊስና በከተማ አስተዳደሩ የንግድ ስርዓቱን ለመቆጣጠርና የዋጋ ንረቱን ለማስተካከል በተቋቋመው ግብረሀይል ነው የተያዙት ተብሏል፡፡
የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ እንደገለፀው÷ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሽሮና በርበሬን ከሰጋቱራ፣ አፈር እና ከሌሎች ጤና ጎጅ አደገኛ ነገሮች ጋር ቀላቅለው በመፍጨት ለገበያ ሊያቀርቡ ነበር፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊ የንግድ ህጉን ጥሰው ሲሰሩ የሚያገኛቸውን ስግብግቦች በየአካባቢው ለተቋቋመው ግብረኃይልና የፀጥታ ኃይል ጥቆማ በመስጠት ራሱን፣ ወገኑንና ሀገሩን ከአሻጥረኞች እንዲታደግ ቢሮው ጥሪ ማቅረቡን ከንግድና ኢንደስተሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.