Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ አገራት ከህዝባቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚሄድ የፖሊሲ አማራጭ መከተል እንደሚገባቸው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣መስከረም 14 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ አገራት ከውጭ የሚጫንባቸውን የፖሊሲ አማራጭ ሳይሆን ከህዝባቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚሄድ አማራጭ ሊከተሉ እንደሚገባ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ባዘጋጀው 4ኛው የቻይና አፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሴሚናር ላይ ተጠቆመ፡፡

ዛሬ በበይነ መረብ በተደረገ ውይይት ላይ የተሳተፉት የብልፅግና ፓርቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ÷በጥልቅ ጥናት ላይ የተመሰረተ አገር በቀል የእድገት ፖሊሲን በመተግበር ብልጽግና ለኢትዮጵያ እድገት መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል፡፡

ባለፉት ሶስት ዓመታት በተተገበረው አገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ በኢትዮጵያ አመርቂ የኢኮኖሚ እድገት መመዝገቡን ዶክተር ቢቂላ ገልጸዋል፡፡

ብልፅግና ፓርቲ በተሳተፈበት በዚህ የቻይና- አፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሴሜናር ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ መቻሏን ጠቅሰው ታላቁን የህዳሴ ግድብን ደግሞ ለማጠናቀቅ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው ባለፉት ሶስት ዓመታት በብልፅግና መሪነት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ሲመዘገብ አሸባሪው ህወሃትና የኮቪድ -19 በሽታ ፈተና እንደነበሩ ነው የገለፁት፡፡

በአንዳንድ የውጭ ኃይሎች ጭምር ድጋፍ የሚደረግለት አሸባሪው ህወሓት አሁንም ድረስ ለአገራችን የእድገት ፀር ሆኖ መቀጠሉን አክለው መናገራቸውን ከብልጽግና ፓርቲ ማህበራዊ ድህረ-ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.