ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የኢትየዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሩዋንዳን 4 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፊፋን ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ውድድር የኢትየዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ርዋንዳን 4 ለ 0 አሸነፈ፡፡
ጎሎቹን ያስቆጠሩት ረድኤት አስረሳኸኝ፣ አረጋሽ ካልሳ እና ቱሪስት ለማ ናቸው፡፡
የፊፋ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ኮስታሪካ 2022 ማጣሪያ ጨዋታዎችም እንደተጠናቀቁ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡