Fana: At a Speed of Life!

የበጋው የዝናብ ስርጭት መደበኛና ከመደበኛ በታች እንደሚሆን ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መጪው በጋ ሊኖር የሚችለው የዝናብ ስርጭት መደበኛና ከመደበኛ በታች መሆኑን የብሔራዊ ሜትዮሮሎጂ ኤጄንሲ ገለፀ።

ኤጄንሲው በመጪው በጋ ሊኖር የሚችለውን የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንበያ ዛሬ ይፋ አድርጓል።

በአዳማ ከተማ በተካሄደውና ባለፈው የክረምት ወቅት የአየር ጠባይና ተጽዕኖው ላይ ባተኮረው የግምገማ መድረክ ላይ

የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ እንደገለፁት በመጪው በጋ የዝናብ ስርጭት መደበኛና ከመደበኛ በታች ነው።

የበጋ ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም ምስራቁ የሀገሪቷ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በታች የዝናብ ስርጭት እንደሚኖራቸው ትንበያው ያሳያል ።

በተለይ የተወሰኑ የደቡብ ክልል አካባቢዎች፣ ቦረና፣ ጉጂ፣ ምስራቅ ባሌና ባሌ ዞን እንዲሁም በሶማሌ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የመጪው በጋ ዝናብ ስርጭት ከሚጠበቀው በታች እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል።

በዚህም ሁሉም የባለድርሻ አካላት ሊኖር የሚችለውን ተፅዕኖ ለመቀነስ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ የቅድመ ዝግጅትና መከላከል ስራላይ መረባረብ አለበት ብለዋል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈጥኖ የሚደርሱ የሰብል ዝሪያዎች፣ የእንስሳት መኖና ድርቅን መቋቋም የሚችሉ ምርጥ ዘር ማዘጋጀትና ፈጥኖ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የአሁኑ የዝናብ ስርጭት እስከ ጥቅምት ወር ድረስ የሚዘልቅ በመሆኑ በበጋ ወቅት ቆላማ የሀገሪቷ አካባቢዎች ላይ የከፋ ችግር እንዳይኖር ውሃን መያዝ እንደሚገባም አሳስበዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.