የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በሚዛን ግቢ ያስተማራቸውን ተማሪዎች በነገው ዕለት ያስመርቃል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በሚዛን ግቢ ሲያስተምራቸው የቆየውን ከ1 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች በነገው ዕለት ያስመርቃል፡፡
ተመራቂዎቹ በመደበኛና በተከታታይ በማህበራዊ ሳይንስ ፣በግብርና እና በተፈጥሮ ሃብት እንዲሁም በህግ ትምህርት ክፍል ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡
ከተመራቂዎች ውስጥም 80ዎቹ በ2ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል በነገው እለት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በተለያዩ ምክንያቶች ያልተመረቁ የኢንጂነሪንግ ና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ስኩል ኦፍ ኢንፎርማቲክስ ተማሪዎችን ያስመርቃል፡፡
በዛሬው እለትም ተመራቂ ተማሪዎች የአረንጓዴ አሻራ እና የደም ልገሳ መርሃ ግብር አከናውነዋል፡፡
በተመሳሳይ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ህግ ትምህርት ቤት ዛሬ 60 የህግ ተማሪዎችን በባችለር ድግሪ አስመርቋል::
ከተመራቂዎቹ ውስጥም 20 ዎቹ ሴቶች መሆናቸው ታውቋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ጉዳይ ዲን እና ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ ተመራቂዎች ፍትህ ለናፈቀው ማህበረሰብ ትክክለኛውን ፍርድ በመሥጠት ማህበረሰቡን ማገልገል እንዳለባቸው ተናግረዋል።
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህር ቤት ዲን መምህር አቢዮት ደስታ በበኩላቸው÷ ሀገሪቱ ሀቀኛ የህግ ባለሙያ ያስፈልጋታል ይህን ደግሞ ከተመራቂ ተማሪዎች እንጠብቃለን ብለዋል።
በዘረአይቆብ ያዕቆብና በአብዱረህማን መሀመድ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!