Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል በዓል በሰላም መጠናቀቁን የጎንደር ከተማ ፖሊስ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ የመስቀል በዓል በሰላም መጠናቀቁን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አየልኝ ታክሎ አስታዋቁ፡፡
ዛሬ በጎንደር ከተማ የተከበረው የመስቀል በዓል በሰላም መጠናቀቁን ኮማንደሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል።
በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ በተለያዩ አደረጃጀቶች የተሳተፉ ወጣቶች በሙሉ ኃላፊነት ስሜት በፍተሻና በማስተባበር ስራ የማይተካ አበርክቶ ነበራቸው ብለዋል፡፡
ለዚህም በጎ ተግራቸውም በጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስም ኮማንደር አየልኝ ታክሎ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.