Fana: At a Speed of Life!

በህወሓት የተያዙ የአማራ ክልል አካባቢዎችን በአጠረ ጊዜ ነፃ ለማውጣት እንሠራለን-የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወራሪው የህወሓት የሽብር ቡድን የተያዙ የአማራ ክልል አካባቢዎችን በህልውና ዘመቻው በአጠረ ጊዜ ነፃ ለማውጣት በትኩረት እንደሚሰሩ አዲሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፍለ ገለፁ፡፡
በህልውና ዘመቻው ወራሪውን ቡድን አቁስሎ መተው ብቻ ሳይሆን÷ ስጋት እንዳይሆን ማድረግ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳደሩ ለአማራ ክልል ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር አመልክተዋል፡፡
የወራሪው ቡድን በሰሜን ወሎ፣ ዋግ ኸምራ እና ሰሜን ጎንደር ወረራውን በመፈፀም የአማራን ህዝብ ቅስም ለመስበር ያደረገውን ጥረት መላ የክልሉ ህዝብ በአንድነት በመቆም ህልውናውን ለማስከበር አኩሪ ጀብዱ በመፈፀም አንድነቱን አሳይተዋል ብለዋል፡፡
ወራሪው የሽብር ቡድን እየፈፀመ ያለው ጭፍጨፋ፣ ማፈናቀል እና ንብረት ማውደም የአማራ ክልል ህዝብ አንድነት እንዲቆም ከማድረጉ ባሻገር፣ የኢትዮጵያን አንድነት ለማስከበር የቆመ መሆኑን በህልውና ዘመቻው በግልፅ ማሳየቱንም ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ ተናግረዋል፡፡
የአማራ ህዝብ ህልውና እና ክብር የሚረጋገጠው ከሌሎች ወንድም ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆኑ ለዚህ ትኩረት ሰጥቶ ክልሉ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡
የህልውና ዘመቻውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እና ተፈናቃዮችን ለማቋቋም እንዲሁም ድጋፍ ለማድረግ አዲሱ የክልሉ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ይሠራል ማለታቸውን ኢ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.