የግብርና ሚኒስቴር እና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ለመከላከያ ሠራዊት 20 በሬዎችንና ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ የዓይነት ድጋፎችን አበርክተዋል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሰማ ገብረመድኅን ÷ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በቀጣይም ማንኛውንም ዓይነት ድጋፍ ለመስጠት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዘመቻውን ለመደገፍ የ10 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ ÷ ዩኒቨርሲቲው ከ33 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ለማድረግ እየሠራ ሲሆን÷ እስካሁን ድረስ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚጠጋ ድጋፍ ማስረከቡን አስታውቀዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ÷የተለያዩ ተቋማት ለአገር ህልውና ቅድሚያ በመስጠት እያሳዩት ያለው ደጀንነት የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብም አሸባሪውን ሕወሓት ለማስወገድ ማንኛውንም ዓይነት መስዋዕትነት እየከፈለ እንደሚገኝ መገለጹን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!