Fana: At a Speed of Life!

የተሰጠውን ህገ-መንግስታዊ መብት በመጠቀም የጋራ ተጠቃሚነትን ማጠናከር ይገባል – አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተሰጠውን ህገ-መንግስታዊ መብት በመጠቀም የህዝቦችን አብሮ የማደግና የጋራ ተጠቃሚነትን የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ፡፡ የስልጤ ብሔረሰብ ራስን በራስ…

4 ኪሎ ቤተ መንግስት ዙሪያ ያለው መንገድ ባለአንድ አቅጣጫ በመደረጉ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ፖሊስ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 4 ኪሎ ቤተ መንግስት ዙሪያ ባለ ሁለት አቅጣጫ የነበረው መንገድ ባለአንድ አቅጣጫ በመደረጉ አሽከርካሪዎች በደምብ መተላለፍ እንዳይቀጡ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል። መንገዱ ባለአንድ አቅጣጫ እንዲሆን መደረጉን ባለማወቅ…

የ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የዕዳ እፎይታ ስምምነት ላይ ተደርሷል – አቶ አሕመድ ሺዴ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከኢትዮጵያ አበዳሪዎች ኮሚቴ ጋር ሲደረግ በነበረው ድርድር የ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የዕዳ እፎይታ ስምምነት ላይ በመርህ ደረጃ መደረሱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ገለጹ፡፡ ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት የ2017 በጀት ዓመት የ3ኛው ሩብ ዓመት…

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የስልጤ ብሔረሰብ የባህል፣ ታሪክና ቋንቋ ዐውደ ርዕይን መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የስልጤ ብሔረሰብ የባህል፣ የታሪክ እና ቋንቋ ሲምፖዚየምና ዐውደ ርዕይን መርቀው ከፈቱ፡፡ የስልጤ ብሄረሰብ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ህጋዊ እውቅና ያገኘበት 24ኛ ዓመት…

ኢትዮ ቴሌኮም የ5G የሞባይል ኔትወርክ በባሌ ሮቤ እና አሰላ ከተሞች አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) ኔትወርክ ማስፋፊያ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል በዛሬው ዕለት በባሌ ሮቤና አሰላ ከተሞች አገልግሎቱን በይፋ አስጀምሯል፡፡ በተጨማሪም በደቡብ ምስራቅና ደቡብ-ደቡብ ምስራቅ ሪጅኖች…

መምህራን የትምህርት ስብራትን ለመጠገን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ናቸው – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትምህርት ዘርፍ ስብራቱን ለመጠገን እየተደረገ ባለው ሂደት መምህራን ለትውልዱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ዘርፍ የ9 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም…

ሜክሲኮ ከኢትዮጵያ ጋር በግብርና ቴክኖሎጂ ሽግግር በትብብር እንደምትሰራ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የሜክሲኮ አምባሳደር አሊሃንድሮ ኢስቲቪል ጋር ተወያይተዋል፡፡ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት፥ ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመታት በፊት የዝናብ ጥገኛ የነበረውን የስንዴ ልማት በአሁኑ ወቅት በመስኖ በስፋት…

ሁሉን አካታች የሰላም ግንባታ እንዲኖር በትኩረት ይሰራል – ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሴቶች፣ ወጣቶችና ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች በሀገር ሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰራ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) ገለጹ። “ሰላምን ተለማመዱ በሰላም ኑሩ” የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል።…

ፓኪስታን ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው የኢኮኖሚ ዕድገት ለሌሎች አርአያ መሆን እንደሚችል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ከፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር የውጭ ግንኙነት ልዩ አማካሪ ሰይድ ታሪቅ ፋጢሚ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በሀገራቱ ሰላም፣ ብልጽግና እና የዘላቂ ልማት የጋራ ግቦችን ለማሳካት የባለብዙ…

የአሜሪካና ሩሲያ የሁለትዮሽ ውይይት በኢስታንቡል መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁለተኛው ዙር የአሜሪካ እና ሩሲያ ውይይት በቱርክ ኢስታንቡል መካሄድ ጀምሯል፡፡ በአሜሪካ የሩሲያ አምባሳደር አሌክሳንደር ዳርኪቭ እና በአሜሪከ ረዳት ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሶናታ ኮልተር አማካኝነት የተመሩት የሁለቱ ሀገራት ልዑካን ቡድኖች…