Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የስራ ጉብኝት ጅማ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ለሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ ጅማ ከተማ ገብተዋል። ፕሬዚዳንቱ ጅማ አባ ጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።…

ሰሜን ኮሪያ ከሁለት አመት በኋላ ወታደራዊ ትዕይንት አሳየች

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ ከሁለት አመት በኋላ የመጀመሪያውን ወታደራዊ ትዕይንት አሳየች። ባልተለመደ መልኩ ምሽት ላይ በተካሄደው ወታደራዊ ትዕይንት ፒዮንግያንግ ከዚህ በፊት ያልነበራት የረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል ማሳየቷ ተገልጿል። በትዕይንቱ ላይ…

በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ ያለውን ሠላም ለማረጋገጥ በጋራ እንደሚሠሩ የሃገራቱ ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ ያለውን ሠላም ለማረጋገጥ በጋራ እንደሚሠሩ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ ገለጸ፡፡ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ወታደራዊ ልዑክ በድንበር አካባቢ ሠላምን ለማረጋገጥ በሚቻልበት አግባብ በባሕር ዳር…

በሀረሪ ክልል በ78 ሚሊየን ብር ወጪ አስፋልት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል በ78 ሚሊየን ብር ወጪ አስፋልት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ። የመንገድ ፕሮጀክቱ ከሀረር ኤረር በር እስከ ኤረር ወልድያ ያለው መንገድ ነው። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሩ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሚስራ…

የኢትዮጵያን ለውጥ እደግፋለሁ በሚል መሪ ቃል በቦሌ እና የካ ክፍለ ከተሞች የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ለውጥ አደንቃለሁ፤ እደግፋለሁ" በሚል መሪ ቃል በቦሌ እና የካ ክፍለ ከተሞች የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ፡፡ በዛሬው ዕለት ማለዳ 12 ሰዓት ከ30 ጀምሮ የካ እና በቦሌ ክፍለ ከተሞች "የኢትዮጵያን ለውጥ አደንቃለሁ፤ እደግፋለሁ" በሚል…

መልካ አቴቴ ኢሬቻ በቡራዩ ከተማ ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መልካ አቴቴ ኢሬቻ በቡራዩ ከተማ ተከበረ፡፡ በበዓሉ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች፣ ቄሮወች እና ቀሬዎች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡ በበዓሉ ላይ የተገኙ አባ ገዳዎች የኢሬቻ በዓል የብሄር ብሄረሰቦችን…

አርመኒያ እና አዘርባጃን ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ደረሱ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አርመኒያ እና አዘርባጃን በናጎርኖ ካራባህ ግዛት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማሙ፡፡ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሁለቱ ሃገራት በሞስኮ ለ10 ሰአታት ከተወያዩ በኋላ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን…

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በደረሰ የእሳት አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ ቦሌ ሚካኤል አየር አምባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትናንት ምሽት ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአንድ ሰው ላይ ደግሞ ከባድ የቃጠሎ አደጋ ደርሷል፡፡…

የእንጦጦ ፓርክ በይፋ ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንጦጦ ፓርክ በይፋ ተመረቀ፡፡ ፓርኩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መርቀው ከፍተውታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ በፓርኩ በተለያዩ የስራ መስኮች ለተሰማሩ ድርጅቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ…

ጠ/ሚ ዐቢይ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ፡፡ ውይይቱ በዋናነት በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡…