Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የ2020 የኖቤል የሰላም ሽልማት በማሸነፉ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዓለም የምግብ ፕሮግራም የ2020 የኖቤል የሰላም ሽልማት በማሸነፉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የደስታ መልዕክት ለፕሮግራሙ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ…

በአዲስ አበባ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በማጠር ለተለያዩ አገልግሎት ባዋሉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በማጠር ለተለያዩ አገልግሎት ባዋሉ አካላት ላይ ህጋዊ እርማጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡   የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በመመደብ…

ሰሜን ኮሪያ ትልቅ የተባለውን ወታደራዊ ትዕይንት ልታሳይ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ በታሪኳ ትልቅ የተባለውን ወታደራዊ ትዕይንት ለማሳየት እየተዘጋጀች መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ ወታደራዊ ትዕይንቱ የሠራተኞች ፓርቲን 75ኛ ዓመት ምስረታን በማስመልከት የሚካሄድ ነው ተብሏል፡፡ ለአሁኑ ወታደራዊ ትዕይን ካለፈው…

13ኛው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን የፊታችን ሰኞ ይከበራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 13ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ በዓል ሰኞ ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም "ሰንደቅ ዓላማችን ለሰላማችን፣ ለአብሮነታችንና ለሃገራዊ ብልጽግናችን!" በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገለጸ፡፡ ቀኑ በየዓመቱ የተለያየ መሪ ቃል እየተቀረፀለት በፌደራል፣…

በአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና ደህንነት ፖሊሲ ምክትል ፕሬዚዳንት የተመራው ከፍተኛ የህብረቱ ልዑክ ሶማሌ ክልል ገባ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና ደህንነት ፖሊሲ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆሴፕ ቦረል ፎንትለስ የተመራው ከፍተኛ የህብረቱ ልዑክ ሶማሌ ክልል ገብቷል። ልዑኩ ጅግጅጋ ከተማ ሲደርስ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድና በሌሎች…

ለተላመደ ቲቢ ታካሚዎች የተመጣጠነ ምግብ እየተሰራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለተላመደ ቲቢ ታካሚዎች የተመጣጠነ ምግብ እየተሰራጨ መሆኑን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ አስታወቀ።። ምግቡ እየተሰራጨ የሚገኘው መድሃኒት በተላመደ የቲቢ በሽታ አማካኝነት ሰውነታቸው በምግብ እጦት ለተጎዱ ሕሙማን መሆኑን…

የኢፌዴሪ የፖሊስ ዶክትሪን ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የፖሊስ ዶክትሪን ዛሬ በሸራተን አዲስ ይፋ ሆነ፡፡ ዶክትሪኑ ላለፉት ሁለት ዓመታት በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና በሰላም ሚኒስቴር ሲዘጋጅ የቆየ ነው ተብሏል። የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል ፖሊስ የሕዝብ ሰላም እና ደኅንነት…

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ከኳታር የትራንስፖርት እና ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከኳታር የትራንስፖርት እና ኮሙዩኒኬሽን ሚኒስትር ጃሲም ሲይፍ አህመድ አል ሱላይቲ ጋር ተወያዩ። በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው በዚህ ውይይት ሁለቱ ሀገራት በዘርፉ ያላቸውን ትብብር…

የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል ለማክበር እየተደረገ ባለው ዝግጅት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 15ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል ለማክበር እየተደረገ ባለው ዝግጅት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው። ውይይቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ እና የክልል ምክር ቤት አፈጉባኤዎች በተገኙበት በቢሾፍቱ ነው እየተካሄደ…

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በአየር ንብረት ተጋላጭነት ፎረም የመሪዎች ስብሰባ ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአየር ንብረት ተጋላጭነት ፎረም የመሪዎች ስብሰባ ላይ ተሳተፉ፡፡ የፎረሙ ፕሬዚደንት በሆኑት የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር የተጠራው ስብሰባ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና…