Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

በክልሉ በበልግ ወቅት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በላይ ለምቷል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በበልግ ወቅት ብቻ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር መሬት በላይ ለምቷል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ የግብርና ሽግግር ማረጋገጥ የትኩረት ማዕከል አድርገን…

በሁሉም ዘርፍ አቅምን ማሳደግ የፕሮፌሽናል ሠራዊት መገለጫ ባህሪ ነው – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁሉም ዘርፍ አቅምን ማሳደግ የፕሮፌሽናል ሠራዊት መገለጫ ባህሪ ነው ሲሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለፁ፡፡ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ቢሾፍቱ የሚገኘውን የጦር ሃይሎች ሪፈራል ሆስፒታል በተመረቀበት ወቅት…

የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከል የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለሥልጣን የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሥርጭትን ለመከላከል የጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ። ባለስልጣኑ ባቀረበው በማኅበራዊ ሚዲያ ጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ…

ፊል ፎደን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) - የማንቼስተር ሲቲ አማካይ ፊል ፎደን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2023/24 ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸንፏል፡፡ የ23 ዓመቱ እንግሊዛዊ በውድድር ዓመቱ ለማንቼስተር ሲቲ 17 ጎሎችን ሲያስቆጥር 8 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል፡፡…

አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በታንዛንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግንባታ መሠረተ-ድንጋይ አስቀመጡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በታንዛንያ ዋና ከተማ ዶዶማ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አዲስ ሕንፃ ግንባታ መሠረተ-ድንጋይ አስቀመጡ ። በሌላ በኩል ሚኒስትር ዴኤታዋ ከታንዛንያ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር በጋራ…

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታልን መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቢሾፍቱ የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታልን መርቀው ከፈቱ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በቢሾፍቱ መርቀን የከፈትነው የመከላከያ ሪፈራል ሆስፒታል እጅግ ዘመናዊ…

1 ሺህ 147 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሦስት ዙር በረራ በተከናወነ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 147 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል። በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ከተመለሱት 1 ሺህ 147 ዜጎች ውስጥ 1ሺህ 46ቱ ወንዶች፣ 80 ሴቶች…

ባህርዳር ከተማን ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ለማድረግ እየተሰራ ያለውን ስራ ማጠናከር ይገባል- አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባህርዳር ከተማን ለጎብኚዎችና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ለማድረግ እየተካሄደ ያለው ልማት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አረጋ ከበደ ገለጹ። የባህር ዳር ከተማ የተቀናጀ የመንገድ ዳር ልማትን በተመለከተ በተዘጋጀ ዲዛይን…

ም/ጠ/ ሚ ተመስገን ጥሩነህ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎብኝተዋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን፣…

በትግራይ ክልል ከ845 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ በጀት የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረግ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል መንግስት በመደበው ከ845 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በትግራይ ክልል አምስት ከተሞች የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን በጊዜያዊ አስተዳደሩ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ገለጸ። የምግብ ዋስትና ፕሮግራሙ በመቀሌ፣…