Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤልጅየም ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 21 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤልጅየም ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ዴ ክሮ ጋር ተወያዩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኮፕ28 ጉባኤ አስቀድሞ መወያየታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል። በውይይታቸውም በወቅታዊ…

የዓለም ኤድስ ቀን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ኅዳር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)"የማኅበረሰብ መሪነት ለላቀ ኤች አይ ቪ መከላከል"በሚል መሪ ቃል የዓለም ኤድስ ቀን እየተከበረ ይገኛል። በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው መርሐ-ግብር ÷ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰን ጨምሮ በዘርፉ የሚሠሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ፣…

35ኛው የጉሚ ባላል መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ኅዳር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)-35ኛው የጉሚ ባላል መድረክ “ብዝሃነት እና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ነው። 18ኛው የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ምክንያት በመድረግ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የጫፌ ኦሮሚያ ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ኤሊያስ ሁማታ፣…

በስልጠና የተገኙ ልምዶችን በተግባር ማረጋገጥ ከአመራሩ የሚጠበቅ ቀዳሚ ጉዳይ ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስልጠናዎች የተገኙ ልምዶችን በተግባር ማረጋገጥ ከአመራሩ የሚጠበቅ ቀዳሚ ጉዳይ ነው ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡ አቶ አደም ፋራህ÷ በመቱ ከተማ ለመንግስት አመራሮች እየተሰጠ የሚገኘውን የስልጠና ሒደት እና…

የአክሱም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በየዓመቱ ሕዳር 21 በድምቀት የሚከበረው የአክሱም ጽዮን ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው። በክብረ በዓሉ ላይ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ርዕሰ…

ለኢትዮጵያ ሰላም መረጋገጥ የህዝቦች የነቃ ተሳትፎና የፀጥታ ሃይሉ ቅንጅት ወሳኝ ነው -ሌ/ ጄ ሹማ አብደታ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያ ሰላም መረጋገጥ የህዝቦች የነቃ ተሳትፎና የፀጥታ ሃይሉ ቅንጅት ወሳኝ መሆኑን የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አዛዥ እና የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ዋና ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ገለጹ፡፡ ሌ/ ጄ ሹማ በአማራ ክልል የኦሮሞ…

ለመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ወጥነት ያለው አሰራርና የሕግ ማዕቀፍ ሊዘጋጅ መሆኑ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ የመስኖ ልማት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ያለመ ወጥነት ያለው የአሰራር መስፈርትና የሕግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት የአንድ ዓመት ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል። ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት-ፋኦ በተገኘ…

የፌዴራል ድጎማ በጀት ቀመር ለማሻሻል በሚያስችሉ የቅድመ ዝግጀት ሥራዎች ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበቂ መረጃ የተደገፉ ስራዎችን ማከናወን ለፌዴራል ድጎማ በጀት ቀመር ማሻሻል ሒደት ቁልፍ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሆናቸው ተገለጸ፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ…

ልማት ባንክ የግብርና ዘርፉን በስፋት ለመደገፍ የሚያስችል የወለድ ተመን ማሻሻያ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የግብርና ዘርፉን በስፋት ለመደገፍ የሚያስችል የወለድ ተመን ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ ባንኩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ÷ በግብርና ዘርፍ በአነስተኛ፣ መካከለኛና የኮርፖሬት ፕሮጀክት ብድር 11 ነጥብ 5…

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የመረጃ ክትትልና ትንተና ቡድን መሪ የነበሩት አቶ አቤል እና ነጋዴ የሆኑት አቶ ፉፋ በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀድሞ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የመረጃ ክትትል እና ትንተና ቡድን መሪ አቤል ጌታቸው እና ነጋዴ በሆኑት አቶ ፉፋ ዳባ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የጥፋተኝነት ፍርድ…