Browsing Category
ስፓርት
ወላይታ ድቻ በኢትዮጵያ ዋንጫ ለፍጻሜ አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ሸገር ከተማን 2 ለ 0 በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ወደ ፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል፡፡
ወላይታ ድቻ ለቀጣዩ የውድድር ዓመት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያደገውን ሸገር ከተማን ባሸነፈበት…
በጀርመን በተካሄደው የአዲዳስ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዛሬው ዕለት በጀርመን በተካሄደው የአዲዳስ አዲዜሮ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ተቀዳጅተዋል።
በ5 ኪሎ ሜትር ሴቶች ውድድር አትሌት መዲና ኢሳ ስታሸንፍ÷ በወንዶቹ ዮሚፍ ቀጀልቻ በቀዳሚነት አጠናቀዋል።
ከፍተኛ ፉክክር በተደረገበት…
በወንዶች የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል አትሌት ሳሙኤል ፍሬው አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በወንዶች የ3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ሳሙኤል ፍሬው አሸንፏል።
በቻይና ዢያሚንግ ውድድር አትሌት ሳሙኤል በ8:05.61 በመግባት የቦታው ክብረወሰንና የዓመቱ የርቀቱ ፈጣን ሠዓት በማስመዝገብ በድንቅ ብቃት…
ከ13 ዓመታት ቆይታ በኋላ ከሌስተር ሲቲ ጋር የሚለያየው ጄሚ ቫርዲ…
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሌስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨዋች ጄሚ ቫርዲ ከ13 ዓመታት ቆይታ በኋላ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከሌስተር ሲቲ ጋር እንደሚለያይ ክለቡ አስታውቋል፡፡
ሌስተር ሲቲ በፈረንጆቹ 2015/16 የውድድር ዓመት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ሲያሳካ…
አርሰናልና ክሪስታል ፓላስ ዛሬ ምሽት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ34ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሰናል በሜዳው ኤሚሬትስ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ክሪስታል ፓላስን ያስተናግዳል።
በ66 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አርሰናል ከተከታዮቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማስጠበቅ ከጨዋታው ሙሉ…
“የአሮን ራምሴ እርግማን “
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዌልሳዊው ኢንተርናሽናል የአርሰናል የቀድሞ አማካኝ ተጫዋች አሮን ራምሴ ግብ በሚያስቆጥርባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ አንድ የዓለማችን ገናና ሰው በሠዓታት ልዩነት ሕይዎቱ ያልፋል፡፡
ይህን አጋጣሚ በተደጋጋሚ ያስተዋሉ ጋዜጠኞችም፤ “የአሮን ራምሴ…
ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን እንደማይሳተፍ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በልምምድ ወቅት ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በለንደን ማራቶን እንደማይሳተፍ አስታውቋል፡፡
በሩጫ ሕይወቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚደግፉትና ለሚያበረታቱት አድናቂዎች ምስጋናውን ያቀረበው አትሌት ቀነኒሳ÷ አሁን ላይ…
የዞን አምስት ወርልድ ቴኳንዶ ውድድር ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁሉም የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የተሳተፉበት የዞን አምስት ወርልድ ቴኳንዶ ውድድር መካሄድ ጀምሯል።
የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ያዘጋጀው ይህ ውድድር በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እየተካሄደ ነው።
ውድድሩ በጁንየር፣ በካዴትና በሲንየር…
ሊድስ ዩናይትድ እና በርንሌይ ወደ ፕርሚየር ሊጉ አደጉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሊድስ ዩናይትድ እና በርንሌይ ለ2025/26 የውድድር ዓመት ከሻምፒዮን ሺፕ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ዛሬ በተደረገ የሻምፒዮን ሺፕ ጨዋታ በርንሌይ ሼፍልድ ዩናይትድን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ውጤቱን…
ባሕርዳር ከተማ መቐለ 70 እንደርታን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ባሕርዳር ከተማ መቐለ 70 እንደርታን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የባሕርዳር ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ቸርነት ጉግሳ እና አቤል ማሙሽ በተመሳሳይ ሁለት ሁለት ግቦችን ከመረብ…