Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ዓለምአቀፋዊ ዜና

በፈረንሳይ የተቀሰቀሰው ግጭት እና ሁከት ተባብሶ መቀጠሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ ፖሊስ በአንድ ወጣት ላይ የፈፀመውን ግድያ ተከትሎ የተቀሰቀሰው ግጭት እና ሁከት ተባብሶ መቀጠሉ ተስምቷል፡፡ ግጭቱ አንድ የፖሊስ ኦፊሰር የአልጀሪያ ዜግነት ያለውን የ17 ዓመት ወጣት "ትራፊክ ጥሶ አልፏል" በሚል ተኩሶ መግደሉን ተከትሎ…

ሩሲያ ከምዕራባውን ጋር ለመፎካከር ዝግጁ ናት አሉ ፕሬዚዳንት ፑቲን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በየትኛውም ዘርፍ ከምዕራባውን ጋር ለመፎካከር ዝግጁ ናት ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተናገሩ፡፡ ፕሬዚዳንት ፑቲን“ለመጪው ጊዜ አዲስ ሃሳብ” በተሰኘ ፎረም ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር÷የምዕራውያን ሀገራት በሩሲያ ላይ የጣሉት…

ደብዛዋ ጠፍቶ የነበረው የቲታን ሰርጓጅ ጀልባ ከፊል ስብርባሪ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ“ቲታን” ሰርጓጅ ጀልባ ከፊል ስብርባሪ በዛሬው ዕለት መገኘቱ ተገለጸ፡፡ የአሜሪካ የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች የጀልባዋ የፊት እና የኋላ ክፍል ስብርባሪዎች መገኘቱን ተናግረዋል። በዚህም ካናዳ ሴንት ጆንስ በተባለው አካባቢ ሆራይዘን አርክቲክ…

የኔቶ አባል ሀገራት በዋግነር ጦር ጥቃት ይደርስብናል የሚል ሥጋት አይግባችሁ – ኔቶ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናንትናው ዕለት የዋግነር ቅጥረኛ ወታደራዊ ኃይል ቤላሩስ መግባቱን ተከትሎ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል-ኪዳን ድርጅት(ኔቶ) አባል ሀገራቱን ጥቃት ይደርስብናል የሚል ሥጋት እንዳይገባቸው አሳሰበ፡፡ የኔቶ ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ÷…

ከከሸፈው አመፅ በኋላ የዋግነሩ መሪ ቤላሩስ መግባታቸው ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የዋግነር ቅጥረኛ ወታደራዊ ኃይል ኩባንያ መሥራች እና መሪ ኤቭጄኒ ፕሪጎዢን ቤላሩስ መግባታቸውን የሀገሪቷ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ገለጹ፡፡ ቅዳሜ ዕለት ከከሸፈው አመፅ በኋላ የአማፂያኑ መሪ ቤላሩስ የገቡት ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን…

‘በታሪክ ትልቁ የሐጅ ጉዞ’ በሳዑዲ ዓረቢያ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተያዘው ዓመት የሐጂ ተጓዦች ቁጥር ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን እንደሚልቅ እና በታሪክ ትልቁ ሆኖ እንደሚመዘገብ ተነግሯል፡፡ በትናንትናው ዕለት በሳዑዲ ዓረቢያ መካ የተጀመረው የሐጅ ተጓዦች ዓመታዊ ሥነ-ሥርዓት በቁጥር ከፍተኛ ሑጃጆችን በማስተናገድ…

በካናዳ የተከሰተው ሰደድ እሳት ከ7 ሚሊየን ሄክታር በላይ ደን አቃጠለ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በካናዳ የተከሰተው ሰደድ እሳት እስካሁን 7 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር በላይ ደን ማቃጠሉ ተሰምቷል፡፡ ይህም ክስተቱን እስከ አሁን ታይቶ የማይታወቅ የሰደድ እሳት አደጋ አድርጎታል ነው የተባለው፡፡ ሀገሪቱ ለሰደድ እሳት አደጋ ቅድመ ዝግጅት እና…

ያመፁ የዋግነር ቅጥረኛ ወታደሮችን አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጡ ፕሬዚዳንት ፑቲን አስጠነቀቁ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ያመፁ የዋግነር ቅጥረኛ ወታደሮችን እንደሚቀጡ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስጠነቀቁ፡ የዋግነር ቅጥረኛ ቡድን የሩሲያን ወታደራዊ አመራር ለመጣል መንቀሳቀሱን ከገለጸ ወዲህ ፕሬዚዳንት ፑቲን ለመጀመሪያ ጊዜ መግለጫ…

በሱዳን ያለው ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድ ጊዜ ጋብ ሲል ሌላ ጊዜ ሲፋፋም የሰነበተው የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ግጭት አሁንም በርዕሰ መዲናዋ ካርቱም የተለያዩ አካባቢዎች ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ የተፋላሚዎቹ ግጭት በዋናነት በምሥራቅ ካርቱም፣ ከባሕሪ በስተ ሰሜን እና ከኦምዱርማን በስተ ምዕራብ…

አፍሪካ ለሩሲያ እና ዩክሬን ያቀረበችውን የሠላም ዕቅድ ቻይና እንደምትደግፍ አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ ሩሲያና ዩክሬንን ለማሸማገል የምታደርገውን ጥረት ቻይና እንደምትደግፍ አስታወቀች፡፡ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ ÷ የአፍሪካ መሪዎች የሠላም ተልዕኮ አንግበው ሩሲያና ዩክሬንን ለማሸማገል እያደረጉ ላሉት…