Browsing Category
ዓለምአቀፋዊ ዜና
‘በታሪክ ትልቁ የሐጅ ጉዞ’ በሳዑዲ ዓረቢያ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተያዘው ዓመት የሐጂ ተጓዦች ቁጥር ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን እንደሚልቅ እና በታሪክ ትልቁ ሆኖ እንደሚመዘገብ ተነግሯል፡፡
በትናንትናው ዕለት በሳዑዲ ዓረቢያ መካ የተጀመረው የሐጅ ተጓዦች ዓመታዊ ሥነ-ሥርዓት በቁጥር ከፍተኛ ሑጃጆችን በማስተናገድ…
በካናዳ የተከሰተው ሰደድ እሳት ከ7 ሚሊየን ሄክታር በላይ ደን አቃጠለ
አዲስ አበባ፣ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በካናዳ የተከሰተው ሰደድ እሳት እስካሁን 7 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር በላይ ደን ማቃጠሉ ተሰምቷል፡፡
ይህም ክስተቱን እስከ አሁን ታይቶ የማይታወቅ የሰደድ እሳት አደጋ አድርጎታል ነው የተባለው፡፡
ሀገሪቱ ለሰደድ እሳት አደጋ ቅድመ ዝግጅት እና…
ያመፁ የዋግነር ቅጥረኛ ወታደሮችን አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጡ ፕሬዚዳንት ፑቲን አስጠነቀቁ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ያመፁ የዋግነር ቅጥረኛ ወታደሮችን እንደሚቀጡ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስጠነቀቁ፡
የዋግነር ቅጥረኛ ቡድን የሩሲያን ወታደራዊ አመራር ለመጣል መንቀሳቀሱን ከገለጸ ወዲህ ፕሬዚዳንት ፑቲን ለመጀመሪያ ጊዜ መግለጫ…
በሱዳን ያለው ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድ ጊዜ ጋብ ሲል ሌላ ጊዜ ሲፋፋም የሰነበተው የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ግጭት አሁንም በርዕሰ መዲናዋ ካርቱም የተለያዩ አካባቢዎች ተባብሶ ቀጥሏል፡፡
የተፋላሚዎቹ ግጭት በዋናነት በምሥራቅ ካርቱም፣ ከባሕሪ በስተ ሰሜን እና ከኦምዱርማን በስተ ምዕራብ…
አፍሪካ ለሩሲያ እና ዩክሬን ያቀረበችውን የሠላም ዕቅድ ቻይና እንደምትደግፍ አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ ሩሲያና ዩክሬንን ለማሸማገል የምታደርገውን ጥረት ቻይና እንደምትደግፍ አስታወቀች፡፡
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ ÷ የአፍሪካ መሪዎች የሠላም ተልዕኮ አንግበው ሩሲያና ዩክሬንን ለማሸማገል እያደረጉ ላሉት…
ዩክሬን ወደ ክሬሚያ በሚወስደው ድልድይ ላይ ጥቃት መፈፀሟን ሩሲያ ገለፀች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩክሬን ወደ ክሬሚያ በሚወስደው የኮንሃር ድልድይ ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈፀሟን ሩሲያ ገልፃለች፡፡
“የክሬሚያ መግቢያ” በመባል የሚታወቀው ይህ ድልድይ ክሬሚያን ከሩሲያ እና ከደቡባዊ የኬርሰን ግዛት ጋር የሚያገናኝ ሲሆን በድልድዩ ላይ በተፈጸመው…
9ኛው የአፍሪካ የሕዝብ አገልግሎት ቀን እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘጠነኛው የአፍሪካ የሕዝብ አገልግሎት ቀን ዛሬ በዚምባቡዌ መከበር ጀምሯል።
ቀኑ “ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬታማነት ብቁ የሆነ አህጉራዊ የሕዝብ አስተዳደር ያስፈልጋል” በሚል መሪ ሐሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው።
ለሦስት ቀናት…
ተመድ በሰሜን-ምሥራቅ ናይጄሪያ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለማድረስ 20 ሚሊየን ዶላር መደበ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተመድ በሰሜን-ምሥራቅ ናይጄሪያ አስቸኳይ የምግብ እና የአልሚ ንጥረ-ነገር ድጋፍ ለማድረስ 20 ሚሊየን ዶላር መደበ፡፡
9 ሚሊየን ዶላሩ ከማዕከላዊ የአደጋ ጊዜ ምላሽ የሚገኝ ፈንድ ሲሆን 11 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ ከናይጄሪያ የሰብዓዊ ፈንድ የሚገኝ…
አሜሪካ የታይዋንን መሪ እንዳትቀበል ቻይና ጠየቀች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ኬቨን ማካርቲ የታይዋንን መሪ ዛይ ኢንግ ዌን ተቀብለው እንዳያነጋግሩ ቻይና ጠየቀች፡፡
የታይዋንን መሪ ማነጋገር “የአንድ ቻይና”ን መርኅ እና ሉዓላዊነት መጣስ ነው ብላለች ቻይና፡፡
የቻይና እና የአሜሪካ መሪዎች…
በፈረንጆቹ 2100 የሂማሊያ የበረዶ ግግር 75 በመቶ ሊቀልጥ እንደሚችል ሪፖርት አመላከተ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ 2100 ከሂማሊያ የበረዶ ግግር ውስጥ 75 በመቶው ሊቀልጥ እንደሚችል ተመራማሪዎች አስጠነቀቁ።
በእስያ ሂንዱ ኩሽ ሂማሊያ የሚገኘው የበረዶ ግግር ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየቀለጠ መሆኑንም ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።…