Fana: At a Speed of Life!
Browsing Tag

የተመረጡ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ወሰነ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የሕዝብን ሠላምና ደህንነት ለማስጠበቅ በቀረበው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ…

ከግማሽ ሚሊየን በላይ የመዲናዋ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል። የውኃ ፕሮጀክቶቹ የከተማዋን ዕለታዊ የውኃ ምርት እና ስርጭት እንዲሁም የፍሳሽ ማስወገድ አቅም ከፍ…

የኢትዮጵያ ልብ ሠራዊታችን ነው – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር)

መከላከያ ሠራዊታችን የኢትዮጵያ ጋሻና መከታ፣ ኩራትና ዋስትና ነዉ፡፡ ኢትዮጵያ በሙሉ ክብር፣ ፍቅር እና አንድነት በእያንዳንዱ የመከላከያ ሠራዊታችን አመራር እና አባል ልብ ውስጥ እንዳለች ከተግባርም ከታሪክም አይተናል። ኢትዮጵያ በሠራዊታችን ልብ ውስጥ ያለችው በፍጹም የሀገር ፍቅር መስዋዕትነት ነው።…

በአማራ ክልል የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር ክልሉ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ያጋጠመውን የፀጥታ መደፍረስ በመደበኛ የህግ ማስከበር ስርአት ለመቆጣጠር አዳጋች ሆኖ በመገኘቱ የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ እንዲተገብር የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠየቀ። በክልሉ የተከሰተው የሰላም…

ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር ባላት የጋራ ጉዳይ ላይ ለመተባበር ቁርጠኛ ናት – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር ባላት የጋራ ጉዳይ ላይ ለመተባበር ቁርጠኛ አቋም አላት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀያሺ ዮሺማሳን ጋር ተወያይተዋል፡፡…

ጃፓን በሁለትዮሽና በዓለም አቀፍ ትብብሮች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ቁርጠኝነቷን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀያሺ ዮሺማሳ ሀገራቸው በሁለትዮሽና በዓለም አቀፍ ትብብሮች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ገለጹ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የጃፓኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀያሺ…

የደቡብ ክልል አደረጃጀት ላይ ያተኮረ የውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል አደረጃጀት ላይ ትኩረት ያደረገ የአመራሮች ውይይት በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በውይይት መድረኩ ላይ እንደገለጹት÷ አደረጃጀት በራሱ ግብ ባለመሆኑ የነበረንን የሚያሳጣ ሳይሆን…

ከሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ከ61 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት ከሀገር ውስጥ ጎብኚዎች 61 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽንና የሕዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ አለማየሁ ጌታቸው እንደገለጹት÷ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት…

አቶ ደመቀ መኮንን ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚገባ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአማራ ክልል እየተስተዋሉ ያሉ የጸጥታ ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚገባ ገለፁ፡፡ አቶ ደመቀ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች…

ኢትዮጵያና የአፍሪካ ልማት ፈንድ የ84 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር የልማት ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና የአፍሪካ ልማት ፈንድ ለስንዴ ምርትና ምርታማነት ማሻሻያ የሚውል የ84 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ወይም የ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የልማት ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ ስምምነቱን በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የገንዘብ ሚነስትሩ አቶ አህመድ…