Fana: At a Speed of Life!

በሀላባ ዞን በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን በተከሰተ ከባድ የጎርፍ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡ በዞኑ ዌራ ዲጆ ወረዳ ትናንትና የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ የአምስት ሰዎች ማለፉን የዞኑ አስተዳደር ገልጿል፡፡…

ጊዜው የሚጠይቀውን መስዋዕት ሁሉ ከፍለን የራሳችንን ታሪክ ልንፅፍ ይገባል – ምክር ቤቱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የወረስነውን ታሪክ እየተናገርን የምንኖር ብቻ ሳንሆን ጊዜው የሚጠይቀውን መስዋዕት ሁሉ ከፍለን የራሳችንን ታሪክ በደማቁ ልንፅፍ ይገባል ሲል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስገነዘበ፡፡ ምክር ቤቱ ለ83ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ ቀን…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማዕድ አጋራ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ባስገነባው የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከል የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋራ። አየር መንገዱ ባከናወነው ማዕድ ማጋራት መርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ…

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ጤና ሚኒስቴር ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የጤና ሚኒስቴር ከሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በመተባበር የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት በሰንሻይን ፊላንትሮፊ ፋውንዴሽን አረጋውያን መጦሪያ ማዕከል ለሚገኙ አቅመ ደካሞችና አረጋውያን ማዕድ አጋርተዋል።…

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በጫካ ፕሮጀክት እየሠሩ ላሉ ሠራተኞች የእንኳን አድረሳችሁ መልክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጫካ ፕሮጀክት ላይ እየሠሩ ላሉ ሠራተኞች የእንኳን አድረሳችሁ መልክት አስተላልፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጫካ ፕሮጀክት እየሠሩ ላሉ ሠራተኞች የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀ የምሳ ፕሮግራም…

በፕራግ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቼክ ሪፐብሊክ በተደረገ የፕራግ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ። በወንዶች አትሌት ለሚ ብርሃኑ 2፡08፡45 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ፤ በውድድሩ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሄርጳሳ…

በመዲናዋ ትናንት ምሽት ላይ በእሳት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የትንሳኤ በአል ዋዜማ ምሽት ላይ በእሳት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የመዲናዋ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ ንጋቱ ማሞ እንደገለጹት አደጋው የተከሰተው በቦሌ ክፍለ ከተማ…

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአረጋዊያን እና ለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአረጋዊያን እና ለአቅመ ደካሞች የትንሳኤ በዓልን…

በየአካባቢያችን አቅም ያጠራቸውን ወገኖቻችን ልናስባቸው ይገባል -አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ልብስ ለብሰው ግን ደግሞ ሆዳቸው ባዶ የሆኑ አቅም ያጠራቸውን ወገኖቻችን በየአካባቢያችን ልናስባቸው ይገባል ሲሉ ተናገሩ፡፡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ…

የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል። ባዕሉን በማስመልከት የሃይማኖት አባቶች ባስተላለፉት መልዕክት በዓለ ትንሳኤ የእግዚአብሄር ፍቅር መገለጫና የተስፋችን ማሳያ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል ብለዋል።…