Fana: At a Speed of Life!

ማህበሩ የ7ኛ ሣምንት የዲስፕሊን ውሳኔዎችን ይፋ አድርጓል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ አክሲዮን ማህበር በ7ኛ ሣምንት ጨዋታዎች የተላለፉ የዲስፕሊን ውሳኔዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ በሣምንቱ መርሐ ግብር በተደረጉ ሠባት ጨዋታዎች ስድስቱ በመሸናነፍ እንዲሁም አንድ ጨዋታ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ 16 ጎሎች በ14…

ኳታር ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ ዐቅም ግንባታ ዘርፍ በጋራ ለመሥራት ፍላጎት እንዳላት አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኳታር እና ኢትዮጵያን ግንኙነት በይበልጥ ለማሣደግ በወታደራዊ ዐቅም ግንባታ፣ መሠረተ ልማትና ቴክኖሎጂ መስኮች በጋራ ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው በኢትዮጵያ የኳታር ወታደራዊ አታሼ አስታወቁ፡፡ በኢትዮጵያ የኳታር ወታደራዊ አታሼ ብርጋዲየር ጄኔራል…

በኢትዮጵያ ባሉ የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ከኳታር ባለሃብቶች ጋር ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ከኳታር ባለሃብቶች ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያን ወጪ ምርቶች በመቀበል እና በሀገራችን መዋዕለ-ነዋያቸውን ኢንቨስት በማድረግ…

ወደ ክልሉ ከ203 ሺህ በላይ ኩንታል ማዳበሪያ እየገባ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2016 /17 ዓ.ም የምርት ዘመን የሚውል ከ203 ሺህ በላይ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ መግባት መጀመሩን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ባበክር ሃሊፋ ገለጹ፡፡ በምርት ግብዓት አቅርቦት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ዛሬ በአሶሳ ከተማ…

ከ1 ሺህ 800 ካሬ ሜትር ይዞታ ጋር በተያያዘ በሙስና ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞ የመዲናዋ ከንቲባ አማካሪን ጨምሮ ሌሎች ተከሳሾች ማረሚያ እንዲወርዱ ታዘዘ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 800 ካሬ ሜትር ይዞታን በተለያዩ መጠን ያለአግባብ ግለሰቦች እንዲወስዱ በማድረግና በየደረጃው ይዞታውን ተቀብሎ በመሸጥ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል ተብለው በሙስና ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞ የመዲናዋ ከንቲባ አማካሪን…

ተመድ በ2024 ለሰብዓዊነት የሚውል 46 ቢሊየን ዶላር ያሥፈልገኛል አለ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአዲሱ የፈረንጆቹ ዓመት ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 46 ቢሊየን ዶላር ያሥፈልገኛል ብሏል፡፡ በዛሬው ዕለት የተባለውን ገንዘብ የጠየቀው በዓለምአቀፍ ደረጃ የተንሰራፋውን ግጭት እና መፈናቀል ከግምት ውስጥ በማስገባት…

አንቶኒዮ ጉተሬዝ የኮፕ28 ተደራዳሪዎች ታዳሽ ያልሆኑ የኃይል አማራጮችን እንዲያስቆሙ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ኮፕ28 ታዳሽ ያልሆኑ የቅሬተ አካል ነዳጅን እንዲያስቆም አሳሰቡ፡፡ ዋና ፀሐፊው በዛሬው ዕለት በአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ28) የመጨረሻ ሰዓት ላይ ተደራዳሪዎች…

በመዲናዋ ሕገ-ወጥ ተግባር ሲፈፅሙ በተገኙ 86 የስፖርት ውርርድ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድን ሽፋን በማድረግ ሕገ-ወጥ ተግባር ሲፈፅሙ በተገኙ 86 የስፖርት ውርርድ ( ቤቲንግ) ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለጸ፡፡ የስፖርት ውርርድ ቤቶችን ጨምሮ ጫት መቃሚያና ሺሻ ማጨሻ…

አቶ ደመቀ መኮንን ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዡ ቢንግ ጋር ተወያዩ፡፡ በውይይታቸውም አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ለጀመረችው ሁለንተናዊ የአየር ንብረት ስትራቴጂካዊ አጋርነት…

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ስትራቴጅካዊ አጋርነቷን ለማጠናከር አስተዋጽዖ አለው – አምባሳደር ምስጋኑ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ ስትራቴጅካዊ አጋርነቷን ለማጠናከር አስተዋጽዖ አለው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኳታር 21ኛው የዶሃ ፎረም ላይ…