Fana: At a Speed of Life!

ግብይት ሳይኖር ደረሰኝ ሲሸጡ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀሰተኛ መታወቂያና ስሞችን በመጠቀም የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን አውጥተው ግብይት ሳይኖር ደረሰኝ በመሸጥ ተግባር ላይ ተሰማርተዋል የተባሉ ሥድስት ተጠርጣሪዎች ተያዙ፡፡ ግለሰቦቹ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው…

1 ሺህ 199 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ ችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 199 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ ከተመላሾች ውስጥ 1 ሺህ 159 ወንዶች፣ 19 ሴቶች፣ 21 ጨቅላ ሕጻናት እና 12 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡…

በሲንጋፖር የመንገጫገጭ አደጋ ያጋጠመው አውሮፕላን መንገደኞች 20ዎቹ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲንጋፖር በበረራ ወቅት ከባድ የመንገጫገጭ አደጋ ያጋጠመው አውሮፕላን መንገደኞች መካከል 20ዎቹ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ ተነገረ። አውሮፕላኑ በሲንጋፖር ቻንጊ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲደርስ ታቅዶ የነበረ ሲሆን፥ እስከአሁን ምክንያቱ…

አቶ አሻድሊ ሀሰን ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያዩ። በውይይቱ ርዕሰ መስተዳድሩ÷ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለህዝብ ሰላም እና ልማት ቅድሚያ ሰጥተው…

ኢትዮጵያ በዶሃ የሠራተኛ ዝውውር ዓለም አቀፍ ትስስር መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በኳታር ዶሃ እየተካሄደ በሚገኘው የሠራተኛ ዝውውር ዓለም አቀፍ ትስስር መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡ መድረኩ በባህረ ሰላጤው ሀገራት እና በአፍሪካ ሠራተኛ ላኪ ሀገራት መካከል ያለውን የሰራተኛ ዝውውር ትስስር ለማሳደግ እና በትብብር…

ማክተር ኩባንያ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እንደሚፈልግ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ማክተር የተሰኘው የፓኪስታን ኩባንያ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ መዋዕለ ንዋይ የማፍሰስ ፍላጎት እንዳለው ገለጸ፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከማክተር ኩባንያ ፕሬዚዳንት ዶክተር…

ያልተቆራረጠ የካንሰር የመድሃኒት አቅርቦት እንዲኖር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ያልተቆራረጠ የካንሰር የመድሃኒት አቅርቦት እንዲኖር ጥረት እየተደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የካንሰር መድሃኒቶችን አቅርቦት ለማሻሻል ያለመ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሄዷል፡፡ የጤና ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ደረጄ ድጉማ በዚህ…

የአፍሪካ አንድ ወጥ የአየር ትራንስፖርት ተግባራዊነት እንዲፋጠን እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ አንድ ወጥ የአየር ትራንስፖርት ተግባራዊነት እንዲፋጠን ከባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአፍሪካ አየር መንገዶች ማኅበር አስታወቀ፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ 17 የአፍሪካ ሀገሮች የአህጉሪቱን አንድ ወጥ የአየር ትራንስፖርት…

ኢትዮጵያ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ትልቅ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ትልቅ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። የስትራይድ ኢትዮጵያ ኤክስፖ የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ስራ የእስካሁኑ ሒደት ፈተናዎች እና የቀጣይ እቅዶች ላይ…