Fana: At a Speed of Life!

በዩኒቨርሲቲዎች እየተተገበሩ ያሉ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የዘርፉ ኃላፊዎች በትጋት እንዲሠሩ ተጠየቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ እየተተገበሩ ያሉ ቁልፍ የለውጥ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የዘርፉ ኃላፊዎች በትጋት ሊሠሩ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡ “ከፍተኛ ትምህርት ከፍ ላለ ተጽዕኖ” በሚል መሪ ሐሳብ ሲካሄድ የቆየው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት…

ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣናን ጨምሮ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ100 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጠረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣናን ጨምሮ በ12 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ100 ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡ የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው ዜጎች መካከልም ከ75 በመቶ በላይ ሴቶች መሆናቸው…

ፈረንሳይ ከፓሪሱ ኦሊምፒክ በፊት ተኩስ አቁም እንዲደረግ ለሩሲያ ጥያቄ ልታቀርብ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ ከፓሪሱ ኦሊምፒክ ቀደም ብሎ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ለሩሲያ ጥያቄ ልታቀርብ መሆኑን ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አስታወቁ፡፡ የ2024ቱ የፓሪስ ኦሊምፒክ ከፈረንጆቹ ሐምሌ 26 እስከ ነሐሴ 11 በፈረንሳይ ይካሄዳል፡፡ ይህን ተከትሎም…

አትሌት ጀማል ይመር የራሱን ፈጣን ሠዓት በማስመዝገብ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኮሪያ በተካሄደው የሴዑል ማራቶን አትሌት ጀማል ይመር የራሱን ፈጣን ሠዓት በማስመዝገብ አሸንፏል፡፡ አትሌት ጀማል ውድድሩን ያሸነፈው 2 ሰዓት ከ 6 ደቂቃ ከ8 ሰከንድ በመግባት ሲሆን÷ ይህም የግሉ ፈጣን ሠዓት ሆኖ ተመዝገቧል፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ 18ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ዛሬ በድሬዳዋ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚሁ መሠረት 10:00 ሠዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከሲዳማ ቡና የሚጫወቱ ይሆናል፡፡ እንዲሁም 1:00 ሠዓት ላይ ወላይታ ድቻ እና…

አቶ እንዳሻው ጣሰው ሠላምን ለማፅናት ዘብ መቆም እንደሚገባ አስገነዘቡ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው የሁላችንም ጉዳይ የሆነውን ሠላምን ለማፅናት ዘብ መቆም አለብን ሲሉ አስገነዘቡ፡፡ ርዕሰ መሥተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሠላም ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነው…

ከ15 ሺህ ሴቶች በላይ የተሳተፉበት የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ15 ሺህ ሴቶች በላይ የተሳተፉበት 21ኛ ዙር ቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ በውድድሩም ጉታኒ ሻንቆ 1ኛ፣ ብርነሽ ደሴ 2ኛ እና መቅደስ ሽመልስ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡ መነሻ እና…

በስፔን የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን ላሬዶ ከተማ በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸንፏል፡፡ አትሌት ዮሚፍ ርቀቱን 26 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነው፡፡

የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ችቦ የማብራት ንቅናቄ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ችቦ የማብራት ንቅናቄ በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል። በመጪው ሐምሌ ወር የሚካሄደውን የፓሪስ ኦሎምፒክ ምክንያት በማድረግ ሀገራዊ የኦሎምፒክ ችቦ ማብራት ንቅናቄ መጀመሩ ይታወቃል። በትግራይ ክልል መቀሌ…

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞ…