Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን የትምህርት ግብዓት እየተሠራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል መስከረም 2 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚጀመረው የትምህርት ዘመን የትምህርት ግብዓትና መሠረተ ልማት የማሟላት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የሥርዓተ-ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክተር ወልዶ ሀይሠማ…

የመቀሌና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ መደበኛ ስራዎቻቸው እየተመለሱ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተከስቶ በነበረው ግጭት ምክንያት የመማር ማስተማር ስራቸውን አቋርጠው የነበሩ የመቀሌና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ መደበኛ ስራዎቻቸው እየተመለሱ መሆኑ ተገለጸ። መቀሌ ዩኒቨርሲቲ 2 ሺህ እንዲሁም ራያ ዩኒቨርሲቲ 760…

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ሁለቱ የስራ ሃላፊዎች በክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራት ምቹ ሁኔታዎችን…

የስኳር ፋብሪካዎች በግብዓትና ሌሎች ችግሮች የሚጠበቅባቸውን አላመረቱም ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አብዛኛዎቹ የስኳር ፋብሪካዎች በግብዓት አቅርቦት እጥረት እና በተወሰኑ ፋብሪካዎች አካባቢ በነበረ የጸጥታ ችግር የሚጠበቅባቸው ያህል አለማምረታቸውን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አስታወቀ፡፡ በተጨማሪም ስራዎችን በተቀመጠው መመዘኛ በመስራትና…

በአማራ ክልል የተፈጠረውን ሰላም ማስጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል -የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የተፈጠረውን ሰላም በማስጠበቅ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ሲሉ የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች አጋጥሞ የነበረው የጸጥታ ችግር በሀገር መከላከያና በነዋሪዎች…

አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም አቀፍ የሙስሊም ሊግ ዋና ጸሃፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዓለም አቀፍ የሙስሊም ሊግ ዋና ጸሃፊ ሙሃመድ ቢን አብደል ከሪም አል ኢሳ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በሐይማኖት መቻቻል፣ በሰላም እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ…

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላት ሹመት ፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ፡፡ ሹመቱ የጸደቀው በውሳኔ ቁጥር 17/2015 በ1 ድምፅ ተዓቅቦ እና በአብላጫ ድምፅ መሆኑን የምክር…

ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአዋጅ ቁጥር 1299/2015 በ12 ድምጸ-ተአቅቦ፣ በ16 ታቃውሞ…

የደሴ-ኮምቦልቻ-ከሚሴ-ደብረብርሐን አዲስ አበባ የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለጊዜው ተቋርጦ የነበረው የደሴ-ኮምቦልቻ-ከሚሴ-ደብረብርሐን አዲስ አበባ የየብስ ትራንስፖርት አገልግሎት በዛሬው እለት ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገለፀ። በአንድአንድ የአማራ ክልል አካባቢዎች ሰሞኑን ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት…