Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከላቲን አሜሪካና መካከለኛው እስያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሥፋት እየሠራች ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ ከላቲን አሜሪካና መካከለኛ እስያ ጋር ያላትን የግንኙነት አድማስ ለማስፋት ውጤታማ ሥራዎች እየሠራች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የሚኒስቴሩ ቃል-አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በሰጡት መግለጫ ÷ ኢትዮጵያ ከኮሎምቢያና…

60ኛ ዓመት የአፍሪካ ኅብረት ምሥረታ በዓል ከግንቦት 17 ቀን ጀምሮ ይከበራል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ አንድነት/ኅብረት 60ኛ ዓመት ምሥረታ በዓል ከግንቦት 17 ቀን ጀምሮ እንደሚከበር ተገለጸ፡፡ በዓሉ የአኅጉሩን አንድነት በሚያጠናክሩ መርሐ- ግብሮች እና ዝግጅቶች ላይ እንደሚያተኩር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡…

የኅዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያውያን የልማት አጀንዳ እንጂ የትኛውንም አካል ለመጉዳት ያለመ አይደለም – በዩጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኅዳሴ ግድብ ፕሮጀክቱ ለኢትዮጵያውያን የልማት አጀንዳ እንጂ የትኛውንም አካል ለመጉዳት ያለመ አለመሆኑን በዩጋንዳ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር እፀገነት ይመኑ ገለጹ፡፡ አምባሳደር እፀገነት ይመኑ ከናይል ቤዚን…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝ ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር አብረው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል። በተጨማሪም በተለያዩ ዘርፎች የትብብር…

የቻይና- አፍሪካን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ሴሚናር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና- አፍሪካን ትብብር በአዲስ ዕይታዎች በማዳበር ለማጠናከር ያለመ ሴሚናር በአዲስአበባ እየተካሄደ ነው፡፡ ሴሚናሩ እየተካሄደ ያለው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በስካይ ላይት ሆቴል እየተከበረ ባለበት ሁኔታ…

አመራር በመግደል የአማራ ክልልን ችግር መፍታት አይቻልም – ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ህዝባችንን እናሻግራለን” በሚል መሪ ቃል የአማራ ክልል የከፍተኛና መካከለኛ አመራር ኮንፈረንስ በባህር ዳር ተጀምሯል።   በኮንፈረንሱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር…

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ልዑክ በቻይና ቤጂንግ የተለያዩ ኩባንያዎችን ጎበኘ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ልዑካን ቡድን በቻይና ቤጂንግ በሚገኙ የተለያዩ ኩባንያዎች ጉብኝት አድርጓል፡፡ በዚህ መሰረት ልዑኩ ’ቤጂንግ ኢኮኖሚክ ቴክኖሎጂ ልማት’ የተሰኘ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንን የሥራ እንቅስቃሴ ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡…

የቡድን 7 አባል ሀገራት በሩሲያ ላይ ማዕቀባቸውን ይበልጥ ለማጥበቅ እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምትወስደውን እርምጃ እንድታቆም ለማስገደድ የቡድን 7 አባል ሀገራት ማዕቀባቸውን ይበልጥ ለማጠናከር እየመከሩ ነው፡፡ የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ጉባዔ ከዕለተ አርብ ጀምሮ በጃፓን ሄሮሺማ እየተካሄደ ነው፡፡ ምንም…

ለሱዳን ቀውስ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት 209 ሚሊየን ዶላር ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) በሱዳን በተፈጠረው ቀውስና ሁከት ለተጎዱ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ 209 ሚሊየን ዶላር ያስፈልጋል ብሏል። የሱዳን ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱ በጎረቤት ሀገራትም ላይ ተጥዕኖ እያሳደረ መምጣቱንም…

የኮንስትራክሽን ኤክስፖ እና አውደ ርዕይ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮንስትራክሽን ኤክስፖ እና አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል። በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀውና ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት በሚቆየው ኤክስፖ ከ26 ሀገራት የተውጣጡ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡ ኤክስፖው ለኢትዮጵያ…