Fana: At a Speed of Life!

የኡስታዝ አቡበከር ሁሴንን መኪና ሊነጥቁ ነበር የተባሉ ተከሳሾች ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ታዘዘ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 14 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኡስታዝ አቡበከር ሁሴን የተባለን ግለሰብ በማገት ሊብሬውን በመቀየር መኪናውን ሊነጥቁ ነበር የተባሉ ተከሳሾች ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ታዘዘ። ተከሳሾቹ የተከሰሱበት አንቀጽ ዋስትና የሚያስከለክል መሆኑን ተከትሎ ነው ዋስትናቸው…

በ3 ወራት ከ72 ሚሊየን ዶላር በላይ ከአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ መገኘቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 38 ነጥብ 7 ሺህ ቶን ምርት ወደ ውጭ በመላክ ከአምራች ኢንዱስትሪው ከ72 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ፡፡ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ÷ በሩብ ዓመቱ የኢንዱስትሪው ዘርፍ አበረታች…

ለንደንን ከ2 እጥፍ በላይ የሚበልጥ የበረዶ ግግር ተገምሶ እየሄደ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የለንደንን መጠነ-ሥፋት ከ2 እጥፍ በላይ የሚሆን የዓለማችን ትልቁ የበረዶ ግግር ተገምሶ እየሄደ ነው ተባለ፡፡ የበረዶ ግግሩ በፈረንጆቹ 1986 ላይ ከአንታርክቲክ ባሕር ዳርቻ ተቆርሶ በዌድል ባሕር አካባቢ የቆየ ሲሆን፥ ከመጠኑ ግዝፈት አንጻርም…

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በ3ኛው የፓን አፍሪካ የሰላም ባህል ፎረም ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 14 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በአንጎላ በተካሄደው 3ኛው የፓን አፍሪካ የሰላም ባህል ፎረም ላይ ተሳትፈዋል። ፎረሙ በአፍሪካ ህብረት እና አንጎላ ከተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ጋር በጥምረት የተዘጋጀ መሆኑ…

ኢትዮጵያ ለመበልፀግ በምታደርገው ጉዞ የማዕድን ዘርፉ ወሳኝ ሚና ይጫወታል – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለመበልፀግ በምታደርገው ጉዞ የማዕድን ዘርፉ ወሳኝ ሚናን ይጫወታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ በማዕድን ዘርፍ…

የኢትዮጵያ- ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት 125ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበት 125ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በሩሲያ የባህል ማዕከል ተከብሯል፡፡   ‘ፋውንዴሽን ፎር ክርኤቲቭ ኢኒሺዬቲቭ’ ከሩሲያ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን በአዲስ አበባ የሩሲያ የሳይንስና…

የሃውቲ አማፂያን በእስራኤል መርከብ የፈፀሙት ጥቃት የሳዑዲን የሰላም ጥረት ማስተጓጎሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃውቲ አማፂያን በእስራኤል የንግድ መርከብ ላይ የፈፀሙት ጥቃት ሳዑዲ አረቢያ በየመን የምታደርገውን የሰላም ጥረት ማስተጓጎሉ ተገለፀ፡፡ ባለፈው እሁድ በኢራን ይደገፋሉ የተባሉት የሃውቲ አማፂያን በቀይ ባህር ከቱርክ ወደ ህንድ በመጓዝ ላይ…

የብሔራዊ ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ስትራቴጂ መጽደቅ ማብሰሪያ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአቅም ችግር ምክንያት የሕግ አገልግሎት ማግኘት የማይችሉ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የብሔራዊ ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ስትራቴጂ መጽደቅ ማብሰሪያ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው። በመርሐ ግብሩ ላይ የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ ዓለምአንተ አግደውን…

በክልሉ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አቶ እንዳሻው ጣሰው ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጸጥታ ምክር ቤት ምስረታና በክልሉ ሰላምና ጸጥታ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የጸጥታ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ እንዳሻው…