Fana: At a Speed of Life!

ፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ አመራር የሆኑ የሱፐርቪዢን ቡድን አባላት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት አካሄዱ፡፡ ቡድኑ ለተከታታይ 10 ቀናት በተለያዩ የከተማዋ ክፍለ ከተሞች ፣ ወረዳዎች እንዲሁም እስከ ቤተሰብ ድረስ…

ቻይና እና ሩሲያ ጥምር የባሕር እና የአየር ኃይል የጦር ልምምድ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና እና ሩሲያ ጥምር የባሕር እና የአየር ኃይል የጦር ልምምድ በጃፓን ባሕር ላይ መጀመራቸው ተነገረ። የ"ሰሜኑ ወይም መስተጋብር 2023" የተሰኘው የሁለቱ ሀገራት የጦር ልምምድ ከዓመታዊ የትብብር ዕቅዳቸው ጋር የተጣጣመ መርሐ-ግብር መሆኑን ሲ…

ከ8 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ተከሳሾች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰበታ የጤና ጣቢያ ፕሮጀክት ውል ስምምነት ሳይደረግ ከ8 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ተከሳሾች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ። የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ነው።…

አቶ ደመቀ መኮንን ከቻይና ልዑካን ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ቢሮ ዳይሬክተር ዋንግ ዪ ከተመራው የልዑካን ቡድን ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። ከልዑካን ቡድኑ ጋር…

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጤና ቢሮ አመራሮች የጤና ኤግዚብሽንን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጤና ቢሮ አመራሮች በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ የሚገኘውን አገር አቀፍ የጤና ኤግዚቢሽንን ጎብኝተዋል። አመራሮቹ የጤናውን ዘርፍ ከማዘመንና ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ከመስጠት ረገድ ሀገሪቱ የደረሰችበት ደረጃ…

በመዲናዋ በቀን 1 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች በነገው ዕለት ይመረቃሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በቀን 1 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርቱ የዳቦ ፋብሪካዎች እና የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት በነገው ዕለት ተመርቀው አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ተገለፀ፡፡ በዚህም በነገው ዕለት ሶስት አዳዲስ የዳቦ ፋብሪካዎች እና ሁለት የምገባ…

አቶ ደመቀ በአገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ገለጻ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ገለጻ አደረጉ። አቶ ደመቀ ከፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ጋር በመሆን ነው ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ለአደረጉ…

የቁልቢ ገብርኤል ክብረ-በዓል በሰላም እንዲከበር ዝግጅት መጠናቀቁን ግብረ ኃይሉ አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቁልቢ ገብርኤል ክብረ-በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡ ግብረ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ÷ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ ሐምሌ…

የሶማሌ ክልል የ2016 በጀት ከ38 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ እንዲጸድቅ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል የ2016 በጀት 38 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ እንዲጸድቅ የውሳኔ ሀሳብ ማሳለፉን የክልሉ መንግስት አስታውቋል፡፡ የክልሉ ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የ2016 የክልሉ መንግስት ረቂቅ በጀት 38 ቢሊየን 395…