Fana: At a Speed of Life!

ባለፈው ዓመት የሚያበረታታ የወጪ ንግድ አፈጻጸም እና ቀጥተኛ የውጭ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ጭማሪ ታይቷል -ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፈው ዓመት የሚያበረታታ የወጪ ንግድ አፈጻጸም እና ቀጥተኛ የውጭ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት ጭማሪ መታየቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄዱን በማህበራዊ…

1 ሺህ 41 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ1 ሺህ 41 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡   ከተመላሾቹ ውስጥ 859 ወንዶች፣ 145 ሴቶች እና 37 ህፃናትና እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች…

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እኩል ደረጃ ያላቸው አራት ዋና ከተሞች ይኖሩታል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እኩል ደረጃ ያላቸው አራት ዋና ከተሞች እንደሚኖሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት አስታወቀ። ምክር ቤቱ የብዝኃ ዋና ከተሞች ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከክልሉ ስድስቱም ዞኖች ከተውጣጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር…

“ሐላል የምግብና ቱሪዝም ኤክስፖ” የፊታችን ሰኞ እንደሚጀምር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ”ሐላል” የምግብና ቱሪዝም ኤክስፖ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ ኤክስፖው ‘’ከኢድ እስከ ኢድ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት’’ የሚለው መርሐ -ግብር አካል መሆኑም ነው የተመለከተው፡፡ ኤክስፖውን በርካታ ቀጥር ያላቸው…

በመዲናዋ ባለፈው አንድ ወር ብቻ 31 ሺህ 449 ጥይት እና 47 ክላሽ መያዙን ፖሊስ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ ባለፈው አንድ ወር ብቻ 31 ሺህ 449 የተለያዩ ጥይቶች፣ 47 ክላሽ እና ሽጉጦች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡   የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በሰጡት መግለጫ÷የከተማዋን…

ኢትዮጵያ 90 በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይሏን የምታመነጨው ከንፁህ እና አረንጓዴ የኃይል ምንጮች ነው – አቶ አሕመድ ሺዴ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ 90 በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይሏን የምታመነጨው ከንፁህ እና አረንጓዴ የኃይል ምንጮች መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕምድ ሺዴ ተናገሩ፡፡ የአፍሪካ የአየር ንብረት ተነሳሽነት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ አቶ አሕመድ ሺዴ…

በኦሮሚያ ክልል ከ21 ሺህ በላይ የአቅመ ደካማ ቤቶችን ለመገንባትና ለማደስ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በክልሉ ከ21 ሺህ በላይ የአረጋውያንና አቅመ ደካማ ቤቶችን ለማደስና አዲስ ለመገንባት እየተሠራ መሆኑን የኦሮሚያ ሴቶችና ህሕጻናት ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ሰርካለም…

ዶክተር መሳይ ሃይሉ ከዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሃይሉ ከዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ቦውሬማ ሳምቦ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በዓለም ጤና ድርጅት መካከል…

በአውሮፓ የዘለቀው የጋዝ አቅርቦት ቀውስ ከ“ድጡ” ወደ “ማጡ” እየሄደ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ የዘለቀው የኃይል አቅርቦት ቀውስ ከመሻሻል ይልቅ ከ”ድጡ” ወደ “ማጡ” እየሄደ መሆኑን የአሜሪካን ባንክ ጠቅሶ አንድ ግብይት ላይ መረጃዎችን የሚያወጣ ድረ-ገጽ አስነብቧል፡፡ የሩሲያ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦዎች በመበላሸታቸው ምክንያት…

ለ11 ሆስፒታሎች ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የላቦራቶሪ መሳሪያዎች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሃዮ ስቴት ግሎባል ዋን ሄልዝ ፕሮግራም በአማራና አፋር ክልሎች በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው 11 ሆስፒታሎች ከ9 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የላቦራቶሪ መሳሪያዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ…