Fana: At a Speed of Life!

ከ39 ሺህ በላይ ሃሰተኛ የብር ኖት ወደ ባንክ አካውንቱ ሊያስገባ የሞከረ ተጠርጣሪ እጅ ከፍንጅ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ከ39 ሺህ በላይ ሃሰተኛ የብር ኖት ወደ ባንክ አካውንቱ ሊያስገባ የሞከረ ተጠርጣሪ እጅ ከፍንጅ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋለው…

የቻይና-አፍሪካ ቀንድ ጉባኤ በቀጠናው አንድነትን እና መከባበርን ማስፈን በሚቻልበት አግባብ ላይ በመወያየት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና-አፍሪካ ቀንድ ጉባኤ በቀጠናው አንድነትን እና መከባበርን ለማስፈን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ተጠናቀቀ። የጉባኤውን መጠናቀቅ አስመልክቶ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የቀጠናውን ሠላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ በጋራ…

የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረ-ሰብ አባል ሀገራት ከውጪ የሚገቡ ልባሽ ጨርቆችን እና ጫማዎችን ሊያግዱ መሆኑ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳ እና ቡሩንዲ የልባሽ ጨርቆችንና ጫማዎችን ገቢ ንግድ ሊያግዱ መሆኑ ተነገሯል፡፡ ሀገራቱ በገቢ ንግድ ከውጭ የሚገቡ ልባሽ ጨርቆችንና ጫማዎችን የሚያግዱት የሀገር ውስጥ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎችን እና የጫማ…

የፍትሕ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሰው ሃብት ልማት በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትሕ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሰው ሃብት ልማት በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ አለምአንተ አግደው እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቺፍ ኢንፎርሜሽን ኦፊሰር ጌትነት…

የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል የምክክር መድረክ በይርጋለም ኢንዱስትሪ ፓርክ ተካሂዷል፡፡ የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቢዝነስ ልማት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጴጥሮስ ማርቆስ…

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ታለንት ልማት ኢንስቲትዩት ባለሙያዎችን ማሰልጠን ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ታለንት ልማት ኢንስቲትዩት ግንባታ ተጠናቆ የተመረጡ የፈጠራ ባለሙያዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን ጀምሯል፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ ከፈጠራ ባለሙያዎች ጋር መክረዋል።…

ወደ ሀገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ፍልሰተኞችን መመለስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን ማጠናከር እና ወደ ሀገራቸው መመለስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡ አምባሳደር ብርሃኑ የዓለም አቀፉን…

ለምርት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ከገበያ ላይ ማግኘት አዳጋች ሆኖብኛል -የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማኅበር

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማኅበር ለምርት የሚያስፈልጉኝን ግብዓቶች ከገበያ ላይ ማግኘት አዳጋች ሆኖብኛል አለ፡፡ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች እንደገለጹት÷ በኮቪድ-19 ምክንያት የቆዳ…

ሰው በማገት ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በ15 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰው በማገት ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በ15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት፡፡ ተከሳሹ አቶ መክት ጠጋ የሚባል ሲሆን ፥ ክሱ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ታህሳስ 7 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት አካባቢ በሶሮቃ…

ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ከትናንት ጀምሮ መውሰድ በጀመረው ኦፕሬሽን ጠንካራ አስተማሪ ስራ እየሰራ ነው-ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ከትናንት ጀምሮ መውሰድ በጀመረው ኦፕሬሽን ጠንካራ የማስተማሪያ ስራ እየሰራ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አራተኛውን ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ…