Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅን ለማሻሻል የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አፅድቋል።…

የአፍሪካ ሀገራት የጤና ድንገተኛና ፈጣን ምላሽ ዝግጁነት ኮሚቴ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው የአፍሪካ ሀገራት የጤና ድንገተኛና ፈጣን ምላሽ ዝግጁነት ኮሚቴ ጉባኤ የአፍሪካ ሀገራት የጤና ዘርፍ አመራሮችና የተለያዩ የልማት አጋሮች በተገኙበት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባዔ በጤናው…

ዩክሬን አሜሪካ ሰራሽ ረጅም ርቀት ሚሳኤል ወደ ሩሲያ አስወነጨፈች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩክሬን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሰጡት ፍቃድ መሠረት አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎችን ወደ ሩሲያ ማስወንጨፏን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ዩክሬን ወደ ብሪያንስክ ግዛት ካስወነጨፈቻቸው ሚሳኤሎች አምስቱ በሩሲያ ጦር የከሸፉ መሆኑን…

የኢንተርኔት ሶሳይቲ ፎረም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኢንተርኔት ለመላው ኢትዮጵያውያን" በሚል መሪ ሃሳብ የዘንድሮው የኢንተርኔት ሶሳይቲ ፎረም እየተካሄደ ነው፡፡ በፎረሙ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የኢንተርኔት አስተዳደር ሀላፊዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ሲቪል ማህበረሰብ፣ የቴክኖሎጂ ልሂቃን እንዲሁም…

ኢትዮጵያና እንግሊዝ ለቀጣናው ሰላም በጋራ መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ ለቀጣናው ሰላም እና ደኀንነት መረጋገጥ በጋራ መስራታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከእንግሊዝ የአፍሪካ ቀንድ እና ቀይ ባሕር ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር…

በአማራ ክልል የማዕድን ክምችት፣ ጥናትና ልየታ ለማከናወን ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ስምምነት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ከባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ወሎ እና ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የሥነ-ምድር ካርታ ሥራና የማዕድን ክምችት ጥናትና ልየታ ለማከናወን ስምምነት ላይ ደርሷል። ጥናቱ በ5 ሺህ 254 ካሬ ኪ/ሜትር ላይ…

ኢትዮጵያ ለተመራጩ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፈች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ማስተላለፉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፤ ሶማሊላንድ በቅርቡ ባካሄደችው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ…

ከ355 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ከጥቅምት 29 እስከ ሕዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 355 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች መያዙን አስታወቀ፡፡ ከተያዙት ዕቃዎች መካከል አልባሳት፣…

ኢትዮጵያ ከስዊዘርላንድ ጋር ትስስሯን በማጠናከር በተለያዩ ዘርፎች የመስራት ፍላጎት እንዳላት ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከስዊዘርላንድ ጋር ትስስሯን በማጠናከር በተለያዩ ዘርፎች የመስራት ፍላጎት እንዳላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከስዊዘርላንድ ኮንፌዴሬሽን ረዳት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ስታልደር ጋር በሁለትዮሽ እና…

ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል መታወቂያ ህትመት አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ህትመት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡ ደንበኞቹን የህትመት ጥያቄአቸውን በቴሌብር ሱፐርአፕ በኦንላይን በማከናወን እና ክፍያ በመፈጸም÷ በአዲስ አበባ በሚገኙ 63 የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት…