Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሲዳማ ዘመን መለወጫ - ፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሲዳማ ውብ ባህል መገለጫ የሆነው…

ቡካዮ ሳካ ከረዥም ጊዜ ጉዳት በኋላ ወደ ልምምድ ተመለሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአርሰናሉ ወሳኝ ተጫዋች ቡካዮ ሳካ ከሶስት ወራት ጉዳት በኋላ ወደ ልምምድ መመለሱ ተነግሯል፡፡ ተጫዋቹ ከቡድኑ ጋር ልምምድ መስራቱ የተገለጸ ሲሆን፥ አርሰናል በቻምፒየንስ ሊጉ ከሪያል ማድሪድ ጋር ላለበት ወሳኝ ጨዋታ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡…

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለፍቼ ጫምባላላ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ - ፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያ በብዝሃ ማንነት፣…

ርዕሳነ መስተዳድሮቹ ለፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ፣ የሶማሌ፣ የደቡብ ኢትዮጵያና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች ለሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ…

የፊቼ ጫምባላላ በዓል የሰላም፣ የአንድነትና የአብሮነት በዓል ነው – ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፊቼ ጫምባላላ በዓል የሰላም፣ የአንድነትና የአብሮነት በዓል ነው ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ። የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል ዋዜማ "ፊጣሪ ሃዋሮ" በመባል የሚታወቀው ክብረ በዓል የክልሉ ምክር ቤት…

ኢትዮጵያና ኢራን በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አብሮ ለመስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በኢትዮጵያ ከኢራን አምባሳደር አሊ አክባር ረዜል ጋር ተወያይተዋል፡፡ አቶ መላኩ አለበል በዚህ ወቅት÷ ኢራን ከኢትዮጵያ ካላት ጉልህ የሁለትዮሽ ግንኙነት በተጨማሪ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ኢንቨስትመንትን…

ፍቼ ጫምባላላ የአብሮነት እና የህብረ ብሔራዊነት ነፀብራቅ የሆነ ድንቅ በዓል ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ለፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ አቶ አደም ፋራህ በማህበራዊ ትስስር…

በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውሮፕላኖችን አገልግሎት ላይ ለማዋል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አርቸር አቪዬሽን በተለያዩ ዘርፎች በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውሮፕላኖችን በአየር ትርንስፖርት አገልግሎት ላይ ለማዋል እና በአርቸር ኤር የበረራ…

የፊቼ ጫምባላላ በዓል ዋዜማ “ፊጣሪ ሃዋሮ” በሀዋሳ መከበር ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል ዋዜማ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡ "ፊጣሪ ሃዋሮ" በመባል የሚታወቀው ክብረ በዓሉ በሲዳማ ባህል አዳራሽ…

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከቻይና ብሔራዊ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከቻይና ብሔራዊ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጋር በትብብር ለመስራት ስምምነት አድርጓል። የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አድማሱ ዳምጠው በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ የባህል ዘርፍ አማካሪ ዣንግ ያዌይን እና በቻይና…