Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና ቻይና የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ቻይና በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሠሩ ተገልጿል፡፡ የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ከቻይና የትምህርት ምክትል ሚኒስትር እና የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ተወካይ ው ያን ጋር ተወያይተዋል።…

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን የማስተናገድ አቅም አላት – የካፍ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2029 የሚካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ አቅም እንዳላት የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የቀድሞው የቦትስዋና እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ማክሊን ኮርቴዝ ሌትሺዊቲ ገለጹ።…

ከደንበኛ ሒሳብ ወደ ሌላ ሰው ገንዘብ ያዛወሩ ተከሳሾች እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከባንኩ ደንበኛ ሂሳብ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ወደ ሌላ ግለሰብ አዘዋውረዋል የተባሉ ተከሳሾች እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነባቸው። ተከሳሾቹ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓድዋ ፓርክ ቅርንጫፍ ባንክ ባለሙያ የነበሩት…

‘MI6’  ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር እንደሚጠናክር አረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪታኒያ ‘ሴክሬት ኢንተለጀንስ ሰርቪስ (MI6)’ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርገውን ዘርፈ-ብዙ ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋገጠ፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች እና የብሪታኒያ ‘ሴክሬት ኢንተለጀንስ ሰርቪስ…

ኢትዮጵያ እና ብሪታኒያ በደኅንነት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ብሪታኒያ በሰላም እና ደኅንነት ዘርፍ በትብብር ለመሥራት ተስማሙ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከብሪታኒያ ‘ሴክሬት ኢንተለጀንስ ሰርቪስ (MI6)’ ኃላፊ ሪቻርድ ሙር ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡…

ማዕቀፉ የተፋሰሱን ሀገራት ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጥ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ተፈፃሚ መሆኑ የተፋሰሱን ሀገራት ፍትሐዊ የውኃ ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጥ ተመላከተ፡፡ የውኃ ኃብት ተመራማሪና ባለሙያ ፈቅ አሕመድ ነጋሽ እንዳሉት የስምምነት ማዕቀፉ ዓላማ÷ ዓለም አቀፍ የውኃ ሕግ መርሆዎችን…

ለጎረቤት ሀገራት ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 31 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሦስት ወራት ለጎረቤት ሀገራት ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 31 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡ በበጀት ዓመቱ ባለፉት ሦስት ወራት 6 ሺህ 456 ጊጋ ዋት ሠዓት የኤሌክትሪክ ኃይል…

ጥራት ያለው የዲጂታል ትምህርት ለተማሪዎች ለማድረስ ያለመ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዲጂታል የትምህርት ስርዓት ላይ ከሚሰራው “ለርኒንግ ሉፕ” ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱ በሁለቱ ተቋማት ትብብር ከፍተኛ ጥራት ያለው የዲጂታል ትምህርት ለኢትዮጵያ ተማሪዎች ለማድረስ መሆኑ…

የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኤርትራ ጋር ጥቅምት 21 እና 24 ቀን 2017 ዓ.ም ለሚያደርገው የቻን ማጣሪያ ደርሶ መልስ ጨዋታ ለ23 ተጨዋቾች ጥሪ ቀረበ፡፡ የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ባቀረቡት ጥሪ መሠረት÷ በግብ ጠባቂ ዘርፍ…

ብሪክስ  ባለብዙ ወገን የዓለም ስርዓትን የሚያረጋግጥ ተቋም ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪክስ ባለብዙ ወገን የዓለም ስርዓትን የሚያረጋግጥ የበየነ መንግስታት ተቋም ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሩሲያ ካዛን ከተማ እየተካሄደ ባለው 16ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር÷…