ሰዎችን አግተው ገንዘብ ሲቀበሉ ነበር የተባሉ የአሸባሪው ሸኔ አባላት ክስ ተመሰረተባቸው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ሰዎችን እያገቱ ገንዘብ በመቀበል የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ ነበር የተባሉ ሦስት የአሸባሪው ሸኔ ቡድን አባላት ክስ ተመሰረተባቸው።
ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት ነው።…