Fana: At a Speed of Life!

የአልነጃሺ መስጅድ ጥገና ሥራ በቀጣይ ሳምንት እንደሚጀመር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የታሪካዊው አልነጃሺ መስጅድ ጥገና ሥራ በቀጣይ ሳምንት እንደሚጀመር የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የቱሪዝም ሚስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር በርክ ባራን ጋር በአልነጃሺ መስጅድ ጥገና ሥራ ላይ ተወያይተዋል፡፡…

የብሪክስ አባል ሀገራት የመሬት ምልከታ ሳተላይት አቅም ለጋራ ጥቅም በሚውልበት ጉዳይ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪክስ አባል ሀገራት ብሔራዊ የስፔስ ተቋማት አመራሮች ስብሰባ በሩሲያ ሞስኮ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። በስብሰባው በኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻያል ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ የተመራ ልዑክ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡…

የግብር አሰባሰብ ስርዓቱን ለማሻሻል የተወሰዱ እርምጃዎች ለውጥ አምጥተዋል – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የግብር አሰባሰብ ስርዓቱን ለማሻሻል የተወሰዱ እርምጃዎች ለውጥ ማምጣታቸውን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ። በክልሉ ለግንባር ቀደም ግብር ከፋዮች እውቅናና ሽልማት…

ሣይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ለሀገራዊ ዕድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ – በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሣይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ለሀገራዊ ዕድገትና ማህበራዊ ደህንነት መጎልበት ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ሲሉ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ "በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ያለበት ደረጃ፣ እይታ እና ተስፋዎች" በሚል መሪ…

ም/ጠ/ሚ ተመስገን የምግብና ስርዓተ ምግብ ዕቅዶች አፈጻጸምን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በምግብ እና ስርዓተ ምግብ፣ በሰቆጣ ቃልኪዳን እና በጤና መድህን ላይ የተያዙ ዕቅዶች እና አፈፃፀማቸውን በተመለከተ ዛሬ ከሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። ምክትል ጠቅላይ…

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካቢኔ  በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። ካቢኔው ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የማረሚያ ቤቶች የታራሚዎች ቀለብ ማሻሻያ ላይ ተወያይቷል። በዚሁ ውይይት በክልሉ…

በሜክሲኮ በተከሰተ የመድረክ መደርመስ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሜክሲኮ በተከሰተ የመድረክ መደርመስ አደጋ አንድ ህፃንን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎች ህወታቸው ማለፉ ተገለፀ፡፡ አደጋው የሜክሲኮ ሴንተሪሰት ሲቲዝንስ ንቅናቄ ፓርቲ መሪ ጆርጌ አልቫሬዝ ሜኔዝ በኒኦቮ ሊዮን ግዛት የምርጫ ቅስቀሳ እያደረጉ በነበረበት ወቅት…

ከተረጂነት አስተሳሰብ መላቀቅ ሁለተኛውን የአርበኝነት ምዕራፍ ለማሳካት መሰረት የምንጥልበት ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተረጂነት አስተሳሰብ መላቀቅ ሁለተኛውን የአርበኝነት ምዕራፍ ለማሳካት መሰረት የምንጥልበት ነው ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ፡፡ ‘ከተረጂነት ወደ ምርታማነት፣ ለተሟላ ሀገራዊ ሉዐላዊነትና…

ተማሪ ደራርቱ ለሜሳን የገደለው ግለሰብ በ18 ዓመት እስራት ተቀጣ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችውን ደራርቱ ለሜሳን በጩቤ ወግቶ የገደለው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣተወሰነበት፡፡ አቶ ዮሐንስ መርጋ ኢተቻ የተባለው ግለሰቡ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከጧቱ 2 ሰዓት 45 ሰዓት አካባቢ…

በመዲናዋ በአፈር መደርመስ አደጋ የአንድ ወጣት ህይዎት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ በግንባታ ላይ ከነበረ ህንጻ አጠገብ ያለ ቤት ውሃልክ ተደርምሶ የአንድ ወጣት ህይዎት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ፡፡ አደጋው ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 በተለምዶ የረር ጉሊት ተብሎ በሚጠራ…