Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ወልቂጤ ከተማ በከፍተኛ ሊግ እንዲጫዎት ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ2017 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተሰረዘው ወልቂጤ ከተማ በከፍተኛ ሊግ እንዲጫዎት መወሰኑን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ ወልቂጤ ከተማ ለ2017 የውድድር ዘመን የክለብ ላይሰንሲንግ ምዝገባ እና ሌሎች የተቀመጡ መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ከፕሪሚየር ሊጉ መሰረዙ ይታወሳል፡፡ ክለቡ የውድድር ፈቃድ መስፈርቶችን እንዲያሟላ በተሰጠው ጊዜ መሰረት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር የሚጠይቀውን መስፈርት በማሟላቱ በከፍተኛ ሊግ እንዲጫዎት መደረጉ ተመላክቷል፡፡ በዚህም…
Read More...

ሩበን አሞሪም የማንቼስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፓርቹጋላዊው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማንቼስተር ዩናይትድን በዋና አሰልጣኝነት እንዲመሩ በይፋ ተሹመዋል፡፡ በስምምነቱ መሠረት አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በኦልትራፎድ በፈረንጆቹ እስከ 2027 የሚያቆያቸውን ኮንትራት ፈርመዋል፡፡ ሆላንዳዊው ሩድ ቫል ኒስትሮይ በምክትል አሰልጣኝነት በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት እንደሚቀጥልም ነው…

ባሕር ዳር ከተማ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ባሕር ዳር ከተማ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 0 አሸነፈ፡፡ የባሕር ዳር ከተማን ግቦችም ፍሬው ሰለሞን እና ፍጹም ዓለሙ አስቆጥረዋል፡፡ በተመሳሳይ 1 ሠዓት ላይ በተካሄደው የዛሬ መርሐ-ግብር ዎላይታ ድቻ ሀድያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ ካርሎስ ዳምጠው በ67ኛው ደቂቃ ኳሷን…

በፕሪሚየር ሊጉ ባሕር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና ይገናኛሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚሁ መሠረት ባሕር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና 10 ሠዓት ላይ እንዲሁም ሀድያ ሆሳዕና ከወዎላይታ ድቻ 1 ሠዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ የወጣው መርሐ-ግብር አመላክቷል፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማንቼስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ፡፡ በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት አሰልጣኝ ቴን ሃግ ስኬታማ ጉዞ እያደረጉ አይደለም በሚል ትችት ሲሠነዘርባቸው ቆይቷል፡፡ ቀያይ ሰይጣኖቹ ትናንት ባደረጉት የፕሪሚየር ሊጉ ዘጠነኛ ሣምንት ጨዋታ በዌስት ሃም 2 ለ 1 መሸነፋቸው ይታወሳል፡፡ በክለቡ…

4 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የዓመቱ ምርጥ አትሌት ዕጩ ውስጥ ተካተቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ ታምራት ቶላ፣ ትዕግስት ከተማ እና ሱቱሜ አሰፋ የ2024 ከስታዲየም ውጭ የወንዶች የዓመቱ ምርጥ አትሌት ምርጫ ላይ በዕጩነት ተካተቱ፡፡ አትሌቶቹ በውድድር ዓመቱ በተለያዩ የጎዳና ላይ ውድድሮች ባስመዘገቡት ውጤት ነው ለዕጩነት መካተት የቻሉት። በውድድር ዓመቱ አትሌት ታምራት ቶላ…

አርሰናል እና ሊቨርፑል አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሣምንት ጨዋታ በሜዳው ሊቨርፑልን ያስተናገደው አርሰናል 2 አቻ ተለያይቷል። 1 ሠዓት ከ30 ላይ በተካሄደው ጨዋታ፥ ቡካዮ ሳካ እና ሚኬል ሜሪኖ የመድፈኞቹን ግቦች አስቆጥረዋል። ቨርጅል ቫን ዳይክ እና ሞሐመድ ሳላህ ደግሞ የሊቨርፑልን ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል።…