Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ጥሩነሺ ዲባባ ከ20 ዓመታት በፊት በዛሬዋ ቀን …

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኩራት የሆኑት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና በአጭር እና በረጅም ርቀት እንዲሁም ጥሩነሺ ዲባባ የታዳጊዎች እና የአዋቂዎችን ውድድር በአንድ ጊዜ በማሸነፍ ከ20 ዓመታት በፊት በዛሬዋ ቀን ደማቅ ታሪክ ጽፈዋል፡፡ አትሌት ቀነኒሳ የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮናን በአጭር እና በረጅም ርቀት ያሸነፈው ከ20 ዓመታት በፊት በዛሬዋ ቀን ሲሆን፤ በዚህም ለተከታታይ አራት ዓመታት በማሸነፍ ብቸኛው ሰው መሆን ችሏል፡፡ በሻምፒዮናው የአጭር ርቀት ውድድር ዘርፍ…
Read More...

በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ቡድን ወደ ቻይና አቀና

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፈረንጆቹ ከመጋቢት 21 እስከ 23 ቀን 2025 በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ወደ ቻይና ናንጂንግ ሌሊት ላይ አቅንቷል። ቡድኑ 12 አትሌቶች፣ ሁለት አሰልጣኞች፣ አንድ ቡድን መሪ፣ አንድ የቴክኒክ ቡድን መሪ፣ አንድ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያ እና አንድ ፊዝዮቴራፒስት…

በለንደን ደርቢ አርሰናል ቼልሲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር አርሰናል በሜዳው ኢምሬትስ ቼልሲን አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የአርሰናልን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ሚኬል ሜሪኖ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከአስራ ሁለት ጨዋታዎች በኋላ የማዕዘን ምት ግብ አስቆጥሯል።…

በባርሴሎና ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2025 የባርሴሎና ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ተስፋዬ ድሪባ በአንደኝት ያጠናቀቀ ሲሆን፤ ርቀቱን ለመጨረስም 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ13 ሰከንድ ፈጅቶበታል፡፡ በዚሁ ውድድር አትሌት ተስፋዬን በመከተል ኬንያውያን አትሌቶች ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው…

የ2017 ዓ.ም ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድርን አትሌት ብሬነሽ ደሴ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድርን አትሌት ብሬነሽ ደሴ 1ኛ በመውጣት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡ በውድድሩ አትሌት አብዙ ከበደ 2ኛ እንዲሁም መቅደስ ሽመልስ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ተከታትለው ገብተዋል። የ2017 ዓ.ም ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ…

የካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ምሽት 1 ሠዓት ከ30 ላይ በዌምብሌይ ስታዲየም በሊቨርፑል እና ኒውካስል ዩናይትድ መካከል ይደረጋል፡፡ ሊቨርፑል በግማሽ ፍፃሜው የሰሜን ለንደኑን ክለብ ቶተንሀም ሆትስፐርን አሸንፎ ለፍፃሜ መብቃቱ ይወሳል፡፡ እንዲሁም ኒውካስል ዩናይትድ ሌላኛውን የሰሜን ለንደን ክለብ አርሰናልን አሸንፎ ነው…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2025 የሴዑል ማራቶን በሁለቱም ጾታ በኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡ በዚሁ መሠረት፤ በወንዶች የ2025 ሴዑል ማራቶን አትሌት ሀፍቱ ተክሉ 2 ሠዓት 5 ደቂቃ ከ37 ሠከንድ በመግባት ውድድሩን በበላይነት ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ በተመሳሳይ በሴቶች ምድብ አትሌት በቀለች ጉደታ 2 ሠዓት ከ21 ደቂቃ ከ35…