የጥጥ ምርት አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪዎችን መስፋፋት ተከትሎ የጥጥ ምርት አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲቲዩት አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲቲዩት የጥጥ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሠለ መኩሪያ እንደተናገሩት የኢንዱስትሪዎች መስፋፋት የስራ ዕድል ከመፍጠር አኳያ የተጫወተው ሚና ላቅ ያለ ቢሆንም የጥጥ አቅርቦቱ አነስተኛ በመሆኑ ከፍተኛ ተግዳሮት ሆኖ ቆይቷል፡፡
አገሪቱ ከፍተኛ ጥጥ የማምረት አቅም ያላት ቢሆንም አርሶ አደሩን ጨምሮ የሚመለከተው አካል ለምርቱ ማደግ የሰጠው ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ ለፋብሪካዎች የሚቀርበው ምርት እጥረት እንዳጋጠመው አቶ መሠለ ተናግረዋል፡፡
በወላይታና በጋሞ ዞኖች የሚገኙ አርሶ አደሮች በበኩላቸው የጥጥ ምርቱን በሰፊው የማምረት ዕድል ቢኖራቸውም ተረካቢ ባለማግኘታቸው ወደ ሌላ እርሻ ስራ መሰማራታቸውን ያወሳሉ፡፡
የኢትዮጵያ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዲስትሪ ልማት ኢንስቲቲዩት በወላይታና በጋሞ ዞኖች ጥጥ አምራች አካባቢዎች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የልምድ ልውውጥ ማካሄዳቸውን ደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!