Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም …

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የቀድሞ ታጣቂዎችን በዘላቂነት ማቋቋም የሚያስችል ምክር ቤት በማዋቀር በትኩረት እየተሰራ ነው አለ።
የቢሮው ኃላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የቀድሞ ታጣቂዎቹ የሰላም አማራጭን በመቀበላቸውና በተወሰደ የሕግ ማስከበር ርምጃ የክልሉ ሰላም ከፍተኛ መሻሻል አሳይቷል።
የተከተሉት አቅጣጫ የተሳሳተ መሆኑን ተገንዝበው የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎች በእስካሁኑ ሂደት ከ22 ሺህ በላይ ናቸው ብለዋል።
ሰላምን ምርጫቸው አድርገው የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን የሥነ ምግባርና ሥነ ልቦና ትምህርትና ስልጠናን በመከታተል የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላቸው ማህበረሰቡን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ ነው ያሉት።
ይህን መነሻ በማድረግም በርካታ ታጣቂዎች ሰላምን በመምረጥ በብዛት እየገቡ እንደሚገኝም ኃላፊው ማስረዳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በቅርቡም የሰላም ጥሪን የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎች በደብረ ብርሃን፣ ኮምቦልቻ እና ጎንደር ጊዜያዊ የተሀድሶ ስልጠና ማዕከላት ገብተው ትምህርትና ስልጠና በመከታተል ላይ ይገኛሉ።
በተጨማሪም የክልሉ መንግስት ህዝቡን በማስተባበር ሰላምን ከማስከበር ባሻገር የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሰፋፊ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.